የጨዋታ ቅድመ ዕይታ| ባህርዳር ከተማ ከ ስሑል ሽረ

 

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የመጀመሪያው ዙር ጨዋታዎች በዚህ ሳምንት በሚደረጉ የ15ኛ ሳምንን መርሀ ግብር ፍፃሚያቸውን ሲያገኙ የዚህ መርሀ ግብር አካል የሆነው የሁለቱም ቡድኖች ጨወታ እንደሚከተለው አይተነዋል።

 

በእስካሁኑ ጉዟቸው በሜዳቸው ያልተደፈሩት የጣናው ሞገዶች ካላቸው የሚዳ ጥንካሬ አንፃር ነጥብ ይዘው ለመውጣት የማይቸገሩ ቢሆንም። የተጋጣሚያቸው ወቅታዊ አቋም ግን በቀላሉ እጅ ይሰጣል ተብሎ አይጠበቅም። ጋባዦቹ ግብ የሚያስቆጥረው የፊት መስመራቸውን ተጠቅመው የተጋጣሚ ግብ ይፈትሻሉ ተብሎ ሲጠበቅ። ጣጣሩን የተጋጣሚያቸው ተከላካይ ስፍራ መስበር ፈተና እንደሚሆንባቸው መገመት አያዳግትም። በተጨማሪም ጠንካራ የፊት እና ኋላ መስመር ያላቸው ስሑላውያኖች በቀላሉ እጁ የሚሰጠውን የባህርዳር ከተማ ተከላካይ ስፍራ ባለሜዳዎቹ ትኩረት ሰጥተው በንቃት ካልተጫወቱ ምናልባትም ምህረት የለሽ የተጋጣሚያቸው አጥቂ ስፍራ ኳስ እና መረብን በቀላሉ ሊያገናኝባቸው ይችላል። ባህርዳሮች ባለሜዳቸው ከመሆናቸው ጋር አጥቅተው የመጫወት አማራጫቸውን ያደርጋሉ ተብሎ ሲገመት። በአብዋኛው ግዜ ከመሀል ሜዳ በሚነሱ ሁለተን መስመር የማጥቃት ምርጫ መንገዳቸውን ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል። ስሑል ሽረዎች ከሜዳቸው ውጭ እንደመጫወታቸው መጠን የኋላ መስመራቸውን ዘግተው ጥንቃቄ የታከለበት አጨዋወት በመከተል የሚገኙ አጋጣሚዎችን ወደ ግብ የመቀየር ስልት ይዘው ይገባሉ ተብሎ ይጠበቃል። የጣናው ሞገዶች በጉዳት ፍቅረሚካኤል አለሙ፣ሳላምላክ ተገኝ ሲያጡ። ስሑላውያኑ በጉዳት ዮናስ ግርማይ እና ኃይለአብ ኃ/ስላሴ በቅጣት ዲዲየ ሌብሪ እና ግብ ጠባቂውም ወንደወሰን አሸናፊ በነገው ጨዋታ የማይጠቀሙ ይሆናሉ።

የእርስ በእርስ ግንኙነት

ከዚህ ቀደም ሁለቱም ቡድኖች ሁለት ግዜ ሲገናኙ አንድ አንድ ጊዜ ተሸናንፈዋል። ይህ ጨዋታ በኢንተርናሽናል አርቢትር እየተመራ 9:00 ይጀምራል።

Hatricksport website Editor

Facebook

ሚሊዮን ኃይሌ

Hatricksport website Editor