የጨዋታ ቅድመ – ዕይታ | ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ ወልቂጤ ከተማ

የጨዋታ ቅድመ ዳሰሳ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ ወልቂጤ ከተማ

ጨዋታ: ቅዱስ ጊዮርጊስ ከወልቂጤ ከተማ
የጨዋታ ቀን: እሁድ የካቲት 28/2012
የጨዋታ አርቢተር: ፌደ. አርቢተር አሸብር ሰቦቃ
የጨዋታ ቦታ: አዲስ አበባ ስታድዮም

በሁለተኛው ዙር የመጀመሪያ ሳምንት የእሁድ መርሀግብር የሊጉን መሪ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ ወልቂጤ ከተማ የሚያገናኝ ይሆናል። ፈረሰኞቹ በመጀመሪያው ዙር ባሳዩት የሜዳ ላይ ጠንካራ ብቃት ነገ ለአዲስ አዳጊዎቹ ወልቂጤ ከተማዎች ከባድ ፈተና ሊሆኑ ይችላሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ሜዳውን ለጥጦ በመጫወት እና የመስመር ተጨዋቾቻቸውን በመጠቀም በመጀመሪያው ዙር በርካታ የግብ እድሎችን ማግኘት የቻሉት ፈረሰኞቹ ነገም በተልይ ጋዲስ መብራህቴ ከጉዳቱ ስላገገመ በነገው ጨዋታ ላይ የሚጫወት ከሆነ በመስመር ላይ የሱ እና የአቤል ያለው እንቅስቅሴ ለክትፎዎቹ ተከላካይ ትልቅ እራስ ምታት ሊሂሆን ይችላል።

ፈረሰኞቹ በአንዳንድ ጨዋታዎች በተለይም በመጀመያው ዙር የመጨረሻ ሁለት ጨዋትዎች ላይ አጥቂውን ጌታነህ ከበደ ወደ ውሃላ ሳብ በማድረግ የ10 ቁጥር ሚና ሰጥተውት የፈጠራ ሀላፊነቱን ጫንቃው ላይ ሲጥሉ ተመልክተናል። ጌታነህ ግብ ከማስቆጠር በዘለለ ለጓደኞቹ ለግብ የሚሆኑ ኳሶችን የማቀበል ብቃቱ ጥሩ የሚባል ቢሆንም ተጨዋቹን ውደሃላ ስቦ ማጫወት ከሱ የሚገኙትን ግቦች የሚያሳንሳቸው ሲሆን በተጨማሪም ተፈጥሯዊ 10 ቁጥር ባለመሆኑ የተነሳ ቡድኑ ከፊት ለሚጫወቱት ሁለት አጥቂዎች በቂ የግብ እድል መፍጠር ሲሳነው በተደጋጋሚ ተመልክተናል። ለዚህም ትልቅ ማስረጃ የሚሆነው በ 15ተኛው ስምንት ከአዳማ ከተማ ጋር ያደረጉት ጨዋትው ነው።

ወልቂጤ ከተማዎች ከወራጅ ቀጠናው በ 2 ነጥብ እርቀው በ19 ነጥብ 11ኛ ደረጃ ላይ የሚገኙ ሲሆን በሊጉ በርካታ አዳዲስ ፊት ካሳዩን ቡድኖች አንዱ ናችው። ከቅርብ ሳምንታት ወዲህበፊት መስመር ላይ ድንቅ ብቃቱን እያሳየን የሚገኝው አጥቂው መሀመድ ሁሴን ለፈረሰኞቹ ቀላል የብልትስራ ይሆናል ተብሎ አይጠበቅም።

ወልቂጤዎች ከሜዳቸው ውጪ በተልይ ጠንከር ካለ ቡድን ጋር ሲጫወቱ ወደውሃላ አፈግፍገው ለአጥቂው መሀመድ ሁሴን ኳስን ሸረጅሙ እያሻገሩ የሱን ፍጥነት እና የሰነት ጥንካሬ በመጠቀም የግብ እድልን ለመፍጠር ሲሞክሩ በተደጋጋሚ ተመልክተናል። ለዚህም ሀሳብ ሁነኛ ማስረጃ የሚሆነን በመጀመሪያው ዙር ከኢትዮጵያ ቡና ጋር አዲስ አበባ ስታድዮም ያደረጉት ጨዋታ ሲሆን መሀመድ በረጅም የሚሻገሩለትን ኳሶች በፍጥነት ወደ ሳጥን ውስጥ ይዞ በመግባት ግብ ለመፍጠር ሲሞክር ተስተውሏ። በጨዋትው የተቆጠረችው ብቸኛዋ ግብም በንእድዚህ አይነት ሂደት የተገኘች ናት።

በነገው ጨዋታ ፈረሰኞቹ የሚያሸንፉ ከሆነ መሪነታቸውን የሚያቀጥሉ ሲሆን ከተሸነፉ ግን በ1 ነጥብ በፋሲል ከተማ ተበልጠው ወደ ሁለተኛነት ዝቅ የሚሉ ይሆናል። በአንፃሩ ደግሞ ወልቂጤዎች ነጥብ የሚያገኙ ከሆነ ከአስፈሪው የወራጅ ቀጠና ዞን በሰፊ ነጥብ መራቅ የሚችሉ ይሆናል።

ቅጣት እና ጉዳት – በቅዱስ በጊዮርጊስ  በኩል አስቻለው ታመነ ፤ አቤል እንዳለ ፤ ናትናኤል ዘለቀ ፤ ለዓለም ብርሀኑ እማይኖሩ ሲሆን በወልቂጤ ከተማ በኩል አወል መሀመድ ፤ አዳነ በላይነህ በግል ጉዳይ ምክንያት እንዳማይኖሩ ሲገለፅ በጉዳት ቶማስ ስምረቱ እማይኖር ይሆናል።