የጨዋታ ቅድመ-ዕይታ | ስሑል ሽረ ከ ሲዳማ ቡና

 

ጨዋታ: ስሑል ሽረ ከ ሲዳማ ቡና
የጨዋታ ቀን: አርብ መጋቢት 4/2012
የጨዋታ ሰዓት: 9:00
የጨዋታ አርቢትር: ፌደራል አርቢትር አክሊሉ ደግፌ
የጨዋታ ቦታ: ሽረ ስታድየም

የሽረ ስታድየም መጠነኛ እድሳቱን ማጠናቀቁን ተከትሎ ከስድስት ወራት የመቐለ ቆይታ በኃላ ወደ ሽረ የተመለሱት ስሑል ሽረዎች የዓመቱ የሜዳቸው የመጀመርያ ጨዋታ ሲዳማ ቡናን በማስተናገድ ይጀምራሉ።በስሑል ሽረ ደጋፊዎች በጉጉት የሚጠበቀውን ጨዋታ እንደሚከተለው ዳሰነዋል።

ባሳለፍነው ሳምንት በኢትዮጵያ ቡና ከባድ ሽንፈት ያስተናገዱት ስሑል ሽረዎች ከሽንፈቱ ለማገገም በሜዳቸው በደጋፊያቸው ፊት ሚያደርጉትን ጨዋታ ከማሸነፍ በላይ የተሻላ አማራጭ አይኖራቸውም።በ12ተኛው ሳምንት ሀዋሳ ከተማን በሜዳቸው አስተናግደው ካሸነፋ በኃላ ባካሄድዋቸው 4 ጨዋታዎች 2 ላይ ተሸንፈው፣2 ላይ አቻ መለያየታቸው ተከትሎ ደረጃቸው እያሽቆለቆለ የሄደው ሽረዎች ወደ ወራጅ ቀጠናው ላለመግባት የነገውን ጨዋታ ማሸነፍ ግድ ሚላቸው ይሆናል።

የሳምሶን አየለን ወንበር ከተረከቡ በኃላ የመጀመርያ ጨዋታቸውን ሚያደርጉት አሰልጣኝ ሲሳይ አብርሀም ነገ ይዘውት ሊገቡ ሚችሉትን የጨዋታ አቀራረብ ለመገመት ከባድ ቢሆንም ቡድኑ ከዚህ ቀደም ይከተል የነበረውን ፈጣን የመስመር የማጥቃት እንቅስቃሴን ያስቀጥላሉ ተብሎ ይጠበቃል።ሁለቱ የመስመር አጥቂዎቻቸው ዲድዬ ሌብሪ እና አብዱልለጢፍ መሐመድ እንዲሁም ሁለቱ የመስመር ተከላካዮቻቸው ዐወት ገብረሚካኤል እና ረመዳን የሱፍ ከመስመር እየተነሱ ወደ ውስጥ በሚያሻሙዋቸው ኳሶች የግብ እድሎችን ሚፈጥሩት ስሑል ሽረዎች በነገው ጨዋታ በተመሳሳይ አቀራረብ ደካማውን የሲዳማ ተከላካይ ክፍልን ይፈትናሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ወደ መሀል ሜዳ ተጠግቶ ለመከላከል ሚሞክረው የስሑል ሽረ ተከላካይ ክፍል በነገው ጨዋታ ከጀርባቸው ለሚጣሉ ኳሶች ጥንቃቄ መስጠት ካልቻሉ ለፈጣን የሲዳማ ቡና አጥቂዎች መጋለጣቸው ማይቀር ይሆናል።

ስሑል ሽረዎች ነፃነት ገብረመድህን በአምስት ቢጫ ካርድ በቅጣት የማያሰለፋ ሲሆን የብሩክ ሀዱሽ መግባት እና አለመግባት ነገርም አጠራጣሪ ሆኗል።

አራት ተከታታይ ጨዋታዎችን በማሸነፍ ከመሪዎቹ ጋር ያላቸውን የነጥብ ልዩነት ማጥበብ የቻሉት ሲዳማ ቡናዎች አምና ያጡትን ዋንጫ ለማግኘት ከሜዳቸው ውጪ ነጥብ ይዘው መውጣት ግድ ይላቸዋል።በሊጉ 33 ግቦችን ማስቆጠር የቻለ የማጥቃት እንቅስቃሴ መገንባት የቻሉት አሰልጣኝ ዘርአይ ሙሉ ከነገው ጨዋታ 3 ነጥብ ይዞ ለመውጣት ማጥቃት ላይ መሰረት ያደረገ አጨዋወትን ይከተላሉ ተብሎ ይጠበቃል።በተለይ የመሀል ሜዳ አማካዮቻቸው ዳዊት ተፈራ እና አበባው ዮውሃንስ መሀል ላይ ሚኖራቸው ጥምረት ቡድኑ ከመከላከል ወደ ማጥቃት በሚያደርገው ሽግግር ስኬት ላይ ከፍተኛውን ድርሻ ሚወስድ ይሆናል። ሲዳማ ቡና በጉዳት እና ቅጣት እሚያጣው ተጫዋችች እንደሌለ ታውቋል።