የጨዋታ ቅድመ-ዕይታ| ስሑል ሽረ ከ ሀድያ ሆሳዕና

 

የኢትዮጽያ ፕሪምየር ሊግ 14ኛው ሳምንት ጨዋታዎች ነገ በሚደረጉ ሰባት ጨወታዎች ሲቀጥል፤ስሑል ሽረ ከ ሃድያ ሆሳዕና የሚያገናኘውን ጨዋታ እንደሚከተለው ዳስሰነዋል።

ጨዋታ:- ስሑል ሽረ ከ ሀድያ ሆሳዕና
የጨዋታ ቀን :-እሁድ የካቲት 08/2012
የጨዋታ ቦታ:-ትግራይ ስታድየም
የጨዋታ ሰዓት:-9:00
የጨዋታ አልቢትር፦ ሃብታሙ መንግስቴ

ባሳለፍነው ሳምንት ከሜዳው ውጪ ከድሬዳዋ ከተማ ጋር ነጥብ የተጋራውና በጥሩ አቋም ሚገኘው ስሑል ሽረ በሊጉ የደረጃ ሰንጠረዥ ግርጌ ላይ ያለውን ሀድያ ሆሳዕና በትግራይ ስታድየም ያስተናግዳል።
በታሪካቸው ለመጀመሪያ ግዜ የሚገናኙት ሁለቱም ቡድኖች ሥስት ነጥቡ ለሁለቱም ቡድኖች ካለው አስፈላጊነት አንፃር ብርቱ ፉክክር ሊያሳዩ እንደሚችሉ ይገመታል።

በኘሪሚየር ሊጉ የደረጃ ሰንጠረዥ በ20 ነጥብ 4ተኛ ደረጃ ላይ ሚገኙት ስሑላውያን የተለመደውን መስመር ላይ መሰረት ያደረገ ኣጨዋወት ይዘው ይገባሉ ተብሎ ይጠበቃል። መሀል ላይ ብዙ አማራጮች ያላቸው አሰልጣኝ ሳምሶን አየለ የመስመር አጨዋወታቸው ተገማች እንዳይሆን ከመሀል ሜዳ እድሎችን እንዲፈጥሩ የፈጠራ አቅማቸው ከፍተኛ የሆነ ተጨዋቾችን ወደ ማዳ ማውረድ ግድ ሚላቸው ይሆናል።

በኣንፃሩ ሀድያ ሆሳዕና አዲስ አሰልጣኝ እንደመቅጠራቸው ይዘውት ሊገቡ ሚችሉትን አጨዋወት ለመገመት ከባድ ቢያደርገውም ጥንቃቄ ላይ መሠረት ያደርገ አጨዋወትን በመጠቀም ነጥብ ሚያገኙበትን ዕድል ያመቻቻሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ስሑል ሽረዎች በዘንድሮዉ ፕርሚየር ሊግ ካደረጋቸው ጨዋታዎች ሰባት ግዜ ሜዳው ላይ ተጫውተዋል ከነዚህም አራት ግዜ ሲያሸንፋ አንድ ላይ ተሸንፈው ቀሪዎቹ ሁለት ጨዋታዎች ላይ አቻ ተለያይተዋል። በሰባቱ ጨዋታዎችን ላይ ዘጠኝ ግቦችን ሲያስቆጥሩ ኣምስት ግቦችን አስተናግደዋል።

ሀድያ ሆሳዕናዎች በበኩላቸው ከሜዳው ውጪ ሰባት ጨዋታዎችን ሲያካሂድ አንድ አሸንፈው፣አንድ ነጥብ ተጋርተው የተቀሩትን ኣምስት ጨዋታዎች ተሸንፈዋል።በሰባቱ ጨዋታዎች ላይ ሥስት ግቦችን ሲያስቆጥሩ ኣስራ አምስት ግቦች ተቆጥሮባቸዋል።

ስሑል ሽረዎች ተከላካያቸውን ዮናስ ግርማይን በጉዳት ግብ ጠባቂያቸው ወንድወሰን አሸናፊን በቅጣት ሲያጡ ሀድያዎች በበኩላቸው አብዱልሰመድ አሊን በጉዳት እሚያጡት ይሆናል

Hatricksport website writer

Twitter

ዳዊት ብርሀነ

Hatricksport website writer