የጨዋታ ቅድመ – ዕይታ | ሲዳማ ቡና ከ ወላይታ ድቻ

በሁለተኛው ዙር የሊግ የመጀመሪያ ጨዋታ ሁለቱን የደቡብ ተወካይ ቡድኖች ሲያገናኝ ከወዲሁ በጉጉት ይጠበቃል ::

በነገው እለት በሚካሄደው ይህ ተጠባቂ ጨዋታ ኢንተ.አርቢትር ለሚ ንጉሴ በመሀል ዳኝነት እንደሚመሩት ታውቋል ::

በሊጉ በርካታ ጎሎችን ማስቆጠር የቻሉት ሲዳማ ቡናዎች በአስፈሪው የፊት መስመራቸው ታግዘው የወላይታ ድቻን የተከላካይ ክፍል ሲረብሹ እንደሚውሉ ይጠበቃል ::

ወላይታ ድቻዎች ከገብረ ክርስቶስ ቢራራ ጋር ከተለያዩ በሃላ በአሰልጣኝ ደለለኝ ደቻሳ እየተመሩ በሊጉ ጥሩ ጉዞን በማድረግ ላይ ይገኛሉ ::

በተለይም በወላይታ ድቻ በኩል የተስፋዬ አለባቸው ወደ ሆሳዕና ማምራት በመሀል ክፍሉ ላይ ክፍተት እንዳይፈጥር ሲያሳጋ በፊት መስመር ልይ ድንቅ የውድድር አመት እያሳለፉ የሚገኙት ባዬ ገዛኸኝ እና እዮብ አለማየሁ ጥምረት በሁለተኛው ዙርም የሚጠበቅ ነው ::

በሲዳማ ቡናዎች በኩል በሜዳቸው በሚያደርጎቸው ጨዋታዎች ላይ በመሀል ሜዳ የጨዋታ እንቅስቃሴ ብልጫ በመውሰድ የጎል ማግባት እድሎችን ለመፍጠር ሲሞክሩ ሲታይ ለዚህም የዳዊት ተፈራ ሚና ጉልሁን ሚና ይይዛል :: ከዚህ በተጨማሪ ቡድኑ በመልሶ ማጥቃት በሚደረጉ እንቅስቃሴዎች ላይ ፈጣን የጨዋታ ዘይቤን ሲከተሉ ይስተዋላል::

ሁለቱ ቡድኖች በመጀመሪያው ዙር ሲገናኙ በወላይታ ድቻ የበላይነት መጠናቀቁ የሚታወቅ ነው ::

hatricksport team

Hatricksport team

Facebook

hatricksport team

Hatricksport team