የጨዋታ ቅድመ – ዕይታ | ሰበታ ከተማ ከ ቅዱስ ጊዮርጊስ

ጨዋታ: ሰበታ ከተማ ከ ቅዱስ ጊዮርጊስ
የጨዋታ ቀን: አርብ መጋቢት 4/2012
የጨዋታ አርቢተር: ኢት. አርቢትር ሀ/እየሱስ ባዘዘው
የጨዋታ ቦታ: አዲስ አበባ ስታድዮም

በስራ ቀናት የሚካሄደው የኢትዮጺያ ፕሪምየር ሊግ 17ተኛ ሳምንት ዛሬ የጀመረ ሲሆን በነገው እለት በአዲስ አበባ ስታዲዮም ሰበታ ከተማ እና ቅዱስ ጊዮርጊስ የሚያገናኝ ይሆናል። ከሜዳ ውጪ ነጥብ ማግኘት ከባድ በሆነበት ሊግ ወደ ትግራይ ተጉዞ ከወልዋሎ ከተማ ጋር ሁለት አቻ በመለያየት 1 ነጥብ ይዞ የተመለሰው የውበቱ አባተው ሰበታ ከተማ እንደ አንደኛው ዙር ሁሉ በሜዳው የሚያደርጋቸው ጨዋታዎች ላይ ጠንካራ ተጋጣሚ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል።

ቅዱስ ጊዮርጊስ ምንም እንኳን በሊጉ በፋሲል ከተማ በ 2 ነጥብ እርቆ ሁለተኝነት ደረጃ ላይ ቢቀመጥም በመልበሻ ቤት እና በሜዳ ውስጥ ችግር እየተንገዳገደ ይገኝል። ባሳለፍነው ሳምንት በተዘበራረቀ አጨዋወት በሜዳው እና በደጋፊው ፊት በወልቂጤ ከተማ የ1-0 ሽንፈት መቅመሱም ይታወሳል። ፈረሰኞቹ ባለፉት ሶስት የፕሪምየር ሊግ ተከታታይ ጨታዎች 2 ነጥብን ብቻ ያገኙ ሲሆን ይህም ውጤት ወደ ዋንጫው በሚያደርጉት ግስጋሴ ትልቅ እንቅፋት አስቀምጦባቸው ነው የሄደው። ከውጤቱ ባሻገር በሜዳ ላይ የሚታየው እንቅስቃሴ ይበልጥ ለደጋፊዎቻቸው ተስፋ አስቆራጭ ሆኖ ተገኝቷል።

ፈረሰኞቹ ከአሰልጣኛቸው ሰርጆቪች እንዲሁም የአሰልጣኙን ቡድን ማገዱን ተከትሎ ይዘው የሚቀርቡት የጨዋታ አቀራረብ በጉጉት የሚጠበቅ ይሆናል ::

የአሰልጣኝ ውበቱ ሰበታ ከወራጅ ቀጠናው በ1 ነጥብ እርቆ በ 19 ነጥብ 13ተኛ ደረጃ ላይ ሲገኝየሁለተኛው ዙር ከወራጅ ቀጠናው እርቆ ባደገበት አመት ወደ ብሄራዊ ሊጉ እንዳይመለስ የሞት ሽረት ትግል የሚያደርግበት ነው ተብሎ ይጠበቃል።

ሰበታ በርካታ ልምድ ያላቸውን እና እድሚያቸው የገፋ ተጨዋቾችን የሰበሰበ ሲሆን የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ብዙ መሮጥ የማይጠይቅ የሶምሶማ ሊግ ስለሆን የስብስቡ እድሜ መግፋት ቡድኑ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ አሳርፏል ማለት ይከብዳል። ሆኖም ግን ቡድኑ ከሜዳው ውጪ ያሚያሳየው አቋም በርካታ ነጥቦችን አሳጥቶታል።

በአዲስ የሚመራው የቡድኑ የተከላካይ ክፍል በወረቀት ላይ አስፈሪ የሚመስል ቢሆንም በርካታ ጨዋታዎች ላይ ግብ ሳይቆጠርበት መውጣት ሲሳነው ተመልክተናል። ወደ ፊት ጠጋ ስንል የታደለ መንገሻ ከረጅም ጊዜ ጉዳቱ አገግሞ ወደ ቀደመ አቋሙ መመለስ ቡድኑ ግብ ለመፍጠር የሚያደርገውን ሂደት በአያሌው አግዞታል።

በነገው እለት የሚገናኙት ባለፉት ሁለት ጨዋትዎች ምንም ግብ ያላስቆጠረው ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ግብ የማስቆጠር ችግር የሌለበት ግን ግቦች የሚቆጠሩብት ሰበታ ከተማ ናችው። ውጤቱ ሁለቱም ቡድኖች በወሳኝ ምዕራፍ ላይ የሚገኝ ነጥብ ሰልሆን በጨዋትው ጠንከር ያለ ፉክክር የእናያለን ተብሎ ይጠበቃል።

ሰበታ ከተማ መስዑድ መሀመድን በቤተሰብ ጉዳይ ብቻ የሚያጣ ሲሆን በፈረሰኞቹ በኩል አቤል እንዳለ ፤ ናትናኤል ዘለቀ፤ አብዱልከሪም መሀመድ በጉዳት እንዲሁም ደስታ ደሙ ደግሞ በቅጣት በጨዋታው ግልጋሎት የማይሰጡ ይሆናል።