መነሻ ገጽ ሀዲያ ሆሳዕና የጨዋታ ቅድመ-ዕይታ | ሰበታ ከተማ ከ ሀድያ ሆሳዕና
ሀዲያ ሆሳዕናሰበታ ከተማዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ቅድመ-ዕይታ

የጨዋታ ቅድመ-ዕይታ | ሰበታ ከተማ ከ ሀድያ ሆሳዕና

አጋራ
አጋራ

 

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ12ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ዛሬ ሰኞ) ሁለት ጨዋታዎችን በማስተናገድ ፍፃሜውን በአዲስ አበባ ስታድየም የሚካሄደው የሰበታ ከተማ እና ሀድያ ሆሳዕና ጨዋታ እንደሚከተለው ዳስሰነዋል።

ጨዋታ: ሰበታ ከተማ ከ ሀድያ ሆሳዕና
የጨዋታ ቀን: ሰኞ ጥር 25/2012
የጨዋታ ሰዓት: 9:00
የጨዋታ አርቢትር:
የጨዋታ ቦታ: አዲስ አበባ ስታድየም

በ 12ኛው ሳምንት የሊጉ መርሀ ግብር ሁለቱን አዳጊ ክለቦች እርስ በእርስ የሚያገናኝ ይሆናል ፡፡
ሰበታ ከተማዎች ኳስን በመቆጣጠር በመሀል ሜዳ ላይ ብልጫዎችን በመውሰድ በፊት መስመር አጥቂያቸው ፍፁም ገብረ ማርያም እየተመሩ ጥሩ ጉዞን በማድረግ ላይ ይገኛሉ ፡፡
ሰበታ ከተማዎች በሜዳቸው በሚያደርጓቸው ጨዋታዎች ከሊጉ የመጀመሪያ ሳምንት በኋላ ሽንፈትን አላስተናገዱም ፡፡ በሶስት ጨዋታዎች ላይ ሲያሸንፉ በሁለት ጨዋታዎች ላይ አቻ መለያየት ችለዋል ፡፡

ሀድያ ሆሳዕና ባለፉት ሶስት ጨዋታዎች ድል ማድረግ ተስኗቸው አንድ ነጥብ ብቻ ማግኘት ችለዋል ፡፡
በሊጉ በእስከ አሁኑ ጉዟቸው ማሸነፍ የቻሉት በአንድ ጨዋታ ላይ ብቻ ሲሆን ወልዋሎ አዲግራትን 1 ለ 0 በሆነ ውጤት ያሸነፉበት ጨዋታ ብቸኛው ሆኖ ተመዝግቧል ፡፡
በተለይም የሁለቱን መስመር በአብዛኛው በመጠቀም የማጥቃት እንቅስቃሴን የሚመርጠው የውበቱ አባተ ሰበታ ለሀድያ ሆሳዕና የተከላካይ ክፍል ፈተና እንደሚሆንባቸው ሲጠበቅ በሌላ በከል ሀድያ ሆሳዕናዎች በቢስማርክ የሚመራው የፊት መስመራቸው ለሰበታ ተከላካዮች ፈተና እንደሚሆን ይጠበቃል ፡፡
ሰበታ ከተማ በጨዋታው ድል የሚቀናው ከሆነ በደረጃ ሰንጠረዡ ካሉበት 13ኛ ደረጃ ወደ አምስተኛ ደረጃ ከፍ ማለት ሲችሉ ሀድያ ሆሳዕናዎች ሶስት ነጥብ ቢያገኙ ነጥባቸውን የሚያሻሽሉበትን እድል ይፈጥራሉ ፡፡

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሀምራዊ ለባሾቹ እና የጣና ሞገዶቹ ጣፋጭ ሦስት ነጥብን ወደ ቋታቸው ከተዋል

በሊጉ የሳምንቱ የሁለተኛ ቀን ጨዋታ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ባህርዳር ከተማ ወሳኝ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሲዳማ ቡና ሲሸነፍ በተጠባቂው ጨዋታ መቻል በጎል ፌሽታ ነገሌን ረቷል

በሳምንቱ የመጀመሪያ ቀን ጨዋታ የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና በሀድያ ሆሳዕና ሽንፈት ሲያስተናግድ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

ውጤት ለውጧል የተባለው ዳኛ ተባረረ

በዮሴፍ ከፈለኝ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውጤት ለውጠዋል የተባሉ አርቢትሮችን ወደመጡበት መመለሱን አሁንም ቀጥሏል። ከቀናት...

መቐለ 70 እንደርታዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

ዘርአይ ሙሉ በቴክኒክ አማካሪነት ወደ ፕሪምየር ሊጉ ተመልሷል

አሰልጣኙን ያሰናበተው መቐለ 70 እንደርታ ሌላ ሹመትን ፈፅሟል። በያዝነዉ የዉድድር አመት ደካማ...