የጨዋታ ቅድመ ዕይታ| ሰበታ ከተማ ከ ሀዋሳ ከተማ
ጨዋታ :ሰበታ ከተማ ከ ሀዋሳ ከተማ
የጨዋታ ቀን: ቅዳሜ ጥር 16/5 2012
የጨዋታ ሰአት :9:00
የጨዋታ አርቢተር:ፌዴራል አርቢትር አክሊሉ ድጋፌ
የጨዋታው ቦታ:አዲስ አበባስ ስቴዲየም
የኢትዮጲያ ፕሪምየር ሊግ 10ኛ ሳምንት ላይ ሲደርስ ቅዳሜ እና እሁድ ደግሞ ጨዋታዎቹ ይከናወናሉ ነገ ቅዳሜ ሶስት እሁድ ቀሪ አምስት ጨዋታዎች የሚካሄዱ ይሆናል፡፡ እኛ ደግሞ ነገ አዲስ አበባ ስታዲዮም የሚከናወነው የሰበታ ከተማ እና ሀዋሳ ከተማ ጨዋታ እንደሚከተለው በቅድመ ዕይታ ዳሰሳችን እንደሚከተለው አሰናድተንላችኋል።
በ9ኛው ሳምንት ወደ ትግራይ ተጉዞ በመቀሌ 70እንድርታ 2-1 ሽንፈት ገጥሞት የተመለሰው የአሰልጣኝ ውበቱ አባተ ለሊጉ እንግዳ የሆነው ሰበታ ከተማ ባንፃሩ በሜዳው ወልቂጤን አስተናድዶ 3-1 ያሸነፈውን ሀዋሳ ከተማን ያስተናግዳል።
በ11 ነጥብ 10 ደረጃ ላይ የተቀመጡት የአንጋፋ እና ወጣት ተጫዋቾች ስብስብ በሜዳቸው ጥሩ የጨዋታ እንቅስቃሴ የሚታይባቸው ሰበታዎች አብዛኛውን ነጥብ ያገኙት በሜዳቸው በመሆኑ ከነገው ጨዋታ ሶስት ነጥብ ያገኛሉ ተብሎ ይገመታል። በመስመር ፈጣን የማጥቃት እንቅስቃሴ እና ጥሩ ወቅታዊ የመከላከል አቅም ያላቸውን የእንግዳዎቹ ቡድን ወደ ግብ ለመድረስ የሰበታን አጥቂዎች የሚፈተኑ ይሆናል።
ከኢትዮጲያ ቡና 4-1 ሽንፈት በኋላላ መከላከል ላይ ባመዘነ ተከታታይ ጨዋታ አቻ ወጥቶ በሜዳው 3-1 ወልቂጤን ከጥሩ የጨዋታ መሻሻል ጋር የረታው የአሰልጣኝ አዲሴ ካሳው ሀዋሳ ከተማ ጥሩ አቋም ላይ የሚገኘው ብሩክ በየነ የሰበታዎች የተከላካይ መስመር ይፈትናል ተብሎ ይጠበቃል።
በነገው ጨዋታ ወጣቱ አጥቂ መስፍን ታፈሰ በደረሰበት የጉልበት ጉዳት የነገውም ጨዋታ ሊያመልጠው ይችላል ባንፃሩ እስራኤል እሸቱ ከጉዳት ማገገሙን ተከትሎ በነገው ጨዋታ ሊሰለፍ ይችላል ። ሀዋሳዎች በ13 ነጥብከሰበታ ከተማ በሶስት ደረጃ ከፍ ብለው በሰባተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል።
አስተያየት ይስጡ