የጨዋታ ቅድመ-ዕይታ | መቐለ 70 እንደርታ ከ ባህርዳር ከተማ

 

ዛሬ(ሐሙስ) በተካሄደው የወልቂጤ ከተማ እና አዳማ ከተማ ጨዋታ የጀመረው 17ተኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ነገ(እሁድ) 7 ጨዋታዎችን ሚያስተናግድ ይሆናል።መቐለ 70 እንደርታ ባህርዳር ከተማን ሚያስተናግድበትን ጨዋታ እንደሚከተለው ዳሰነዋል።

ጨዋታ: መቐለ 70 እንደርታ ከ ባህርዳር ከተማ
የጨዋታ ቀን: አርብ መጋቢት 4/2012
የጨዋታ ሰዓት: 9:00
የጨዋታ አርቢትር: ኢንተርናሽናል አርቢትር ቴዎድሮስ ምትኩ
የጨዋታ ቦታ: ትግራይ ስታድየም

የሳምንቱ ተጠባቂ ጨዋታ የሆነው የመቐለ 70 እንደርታ እና ባህርዳር ከተማ ግጥሚያ ነገ በግዙፋ በትግራይ ስታድየም ይካሄዳል።በመሀከላቸው የሁለት ነጥብ ልዩነት ያላቸው ሁለቱም ቡድኖች ነገ ሚያደርጉት ጨዋታ ለዋንጫ በሚደርጉት ጉዞ ላይ ከፍተኛ ድርሻ ሚጫወት ይሆናል።

ሁለተኛው ዙርን ከሜዳቸው ውጪ ሀድያ ሆሳእናን በማሸነፍ የጀመሩት መቐለ 70 እንደርታዎች የአምና ክብራቸውን ለማስጠበቅ የሚያደርጉትን ሩጫ ለማስቀጠል የሜዳቸውን ጨዋታዎች ማሸነፍ ግድ ሚላቸው ይሆናል።በትግራይ ስታድየም 8 ጨዋታዎችን አካሂደው ስድስቱ ላይ አሸንፈው፣አንዱን አቻ ተለያይተው በፋሲል ከነማ የተሸነፋት መቐለዎች ማግኘት ከሚችሉት 24 ነጥብ 19ኙን ማሳካት ችለዋል።

ከጨዋታ ጨዋታ መቀናጀት ሚታይበት የአማኑኤል ገብረሚካኤል እና የኦኪኪ ኦፎላቢ የፊት ጥምረት ላይ መሰረት ያደረገ ቀጥተኛ አጨዋወትን ሚከተሉት ምዐም አናብስቶቹ በነገው ጨዋታም ከመስመር እና ከመሀል መነሻቸውን ባደረጉ ኳሶች እድሎችን ይፈጥራሉ ተብሎ ይጠበቃል።በግማሽ ዓመቱ የተጨዋቾች ዝውውር ላይ ጋናዊውን የአጥቂ አማካይ ካሉሻ አልሀሰን ወደ ቡድናቸው የቀላቀሉት አሰልጣኝ ገብረመድህን ኃይሌ ቡድኑ መሀል ሜዳ ላይ የነበረውን ክፍተት በመጠኑ ሊቀርፍላቸው እንደሚችል ይገመታል።

መቐለ 70 እንደርታዎች አንጋፋው አማካያቸው ሚኪኤለ ደስታ ከጉዳቱ አገግሞ ቀለል ያለ ልምምድ በመስራት ላይ ቢገኝም ለነገው ጨዋታ አይደርስም።በተጨማሪ አዲሱ የቡድኑ ፈራሚ ሙሳ ዳኦም ለነገው ጨዋታ ማይደርስ ይሆናል።

ባሳለፍነው ሳምንት ጅማ አባጅፋር ላይ ድል በመቀዳጀት ከመሪዎቹ ጋር ያላቸውን የነጥብ ልዩነት ማጥበብ የቻሉት ባህርዳሮች ለዋንጫ ከታጩት ቡድኖች ተርታ ውስጥ ለመግባት ከዚህ ጨዋታ ቢያንስ አንድ ነጥብ ይዘው መውጣት ግድ ሚላቸው ይሆናል።የጣና ሞገዶቹ ከሜዳቸው ወጥተው ባደረጉዋቸው 8 ጨዋታዎች አንድም ድል ማስመዝገብ ሳይችሉ ስዱስቱ ላይ ሽንፈት አስተናግደው በቀሪዎቹ ሁለት ጨዋታዎች ላይ አቻ ተለያይተዋል።

መስመር ላይ ትኩረት ያደረገ የማጥቃት እንቅስቃሴ ሚከተሉት ባህርዳሮች በነገው ጨዋታ መልሶ ፍጥነት እና ተጨዋቾችን ቀንሶ የማለፍ ክህሎት ባላቸው ግርማ ዲሳሳ እና ፍፁም አለሙ ላይ ትኩረት ያደረገ የመልሶ ማጥቃት አጨዋወትን መርጠው ሊገቡ እንደሚችሉ ይገመታል።በተጨማሪማ ቡድኑ እንደ ማማዱ ሲሴኮ እና አዳሙ ሲሴኮ የአየር ኳሶችን በአግባቡ መጠቀም ሚችሉ ተጨዋቾችን መያዙ ከቆሙ ኳሶችንም ግብ ለማግኘት አቅደው ሊገቡ ይችላሉ።

ባህርዳር ከተማ ወሰኑ አሊና እና ፍቅረሚካኤል አለሙን በጉዳት የማያገኝ ይሆናል።

Hatricksport website writer

Twitter

ዳዊት ብርሀነ

Hatricksport website writer