የጨዋታ ቅድመ-ዕይታ | ሀድያ ሆሳዕና ከ ወላይታ ድቻ

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 13ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ከቅዳሜ አንስቶ ሲካሄዱ በነገው እለትም የሁለቱን ቡድኖች ጨዋታ ያስተናግዳል።

በዚህ ሳምንት በቅጣት ምክነያት የቦታ እና የቀን ለውጥ ተደርጎበት ከሚካሄዱት ጨዋታዎች መካከል በሀዋሳ ስታዲየም ሀድያ ሆሳዕና ከ ወላይታ ድቻን የሚያስተናግድበት ጨዋታ በጉጉት ይጠበቃል።

ጨዋታ: ሀድያ ሆሳዕና ከ ወላይታ ድቻ
የጨዋታ ቀን: ማክሰኞ የካቲት 03/2012
የጨዋታ ሰዓት: 9:00
የጨዋታ አርቢትር: አሸብር ሰቦቃ
የጨዋታ ቦታ: ሀዋሳ ስታድየም

በገለልተኛ ሜዳ በሚካሄደው በዚህ መርህ ግብር ሀድያ ሆሳዕና ከገባበት የውጤት ቀውስ ለመውጣት ይረዳው ዘንድ አሰልጣኝ ፀጋዬ ኪዳነ ማርያምን ለመቅጠር ችሏል ::

አሰልጣኝ ፀጋዬ ኪዳነማርያም የመጀመሪያ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ ተብሎ በሚጠበቅበት መርሀ ግብር ሀድያ ሆሳዕናዎች ከሰበታ ከተማው ሽንፈት በማገገም በሜዳ ላይ እንቅስቃሴ ጥሩ ጨዋታን እነሚያሳዩ ይጠበቃል ::

ሀድያ ሆሳዕና ያለፉትን በሊጉ ካደረጓቸው ሶስት ጨዋታዎች ሲሸነፉ በደረጃው ሰንጠረዥ ግርጌ ላይ ሲገኙ ከወዲሁ በወራጅ ቀጠናው ከሚገኘው ድሬድዋ ከተማ በአራት ነጥቦች እርቀው ሲገኙ ከወላይታ ድቻ ጋር የሚያደርጉት ጨዋታም ከሌሎች ቡድኖች በነጥብ እንዳይርቁ ወሳኝ ጨዋታ እንደሚሆን ይጠበቃል ::

ወላይታ ድቻ ከአሰልጣኝ ገብረ ክርስቶስ ቢራራ ጋር ከተለያየ በሃላ በምክትል አሰልጣኙ ደለለኝ ደቻሳ እየተመራ ከገባበት የውጤት ቀውስ በመውጣት ዳግም ተፎክካሪነታቸውን እያሳዩ ይገኛሉ ::

ወላይታ ዲቻ ባለፉት ሶስት ጨዋታዎች ሁለቱን ሲያሸንፉ በአንዱ ተሸንፈው ማግኘት ከሚገባቸው ዘጠኝ ነጥብ ስድስቱን በመሳካት ዌ ቀድሞው አስፈሪነትቸው እየተመለሱ ይገኛሉ ::

በጉዳት ምክንያት በወላይታ ድቻ በኩል ያሬድ ዳዊት በሀዲያ ሆሳዕና በኩል አብዱልሰመድ አሊ በጉዳት ጨዋታው እንደሚያመልጣቸው ተገልጿል ::

ሀድያ ሆሳዕናዎች በጨዋታው ድል የሚቀናቸው ከሆነ በወራጅ ቀጠናው ከሚገኙት ቡድኖች ጋር ያላቸውን የነጥብ ልዩነት ማጥበብ ሲችሉ ወላይታ ዲች ከሜዳው ውጪ ሶስት ነጥብ ይዘው መመለስ የሚችሉ ከሆነ
በደረጃ ሰንጠረዡ እስከ ስምንተኛ ደረጃ ከፍ ማለት የሚችሉበት ውጤት ይዘው ይመለሳሉ ::

 

Hatricksport website Editor

Twitter

kidus Yoftahe

Hatricksport website Editor