የጨዋታ ቅድመ-እይታ | መቐለ 70 እንደርታ ከ ሀዋሳ ከተማ

14ኛው ሳምንት የኢትዮጲያ ፕሪምየር ሊግ በሳምንቱ መጨረሻ ቅዳሜ እና እሁድ እንዲሁም ሰኞ በሚደረጉ 8 ጨዋታዎች ቀጥሎ ይውላል።መቐለ 70 እንደርታ በሜዳው ትግራይ ስታድየም ሀዋሳ ከተማን ሚያስተናግድበትን ጨዋታ በዚህ መልኩ ዳሰነዋል።

ጨዋታ: መቐለ 70 እንደርታ ከ ሀዋሳ ከተማ
የጨዋታ ቀን: ቅዳሜ የካቲት 7/2012
የጨዋታ ሰዓት: 9:00
የጨዋታ አርቢትር: ኢንተርናሽናል አርቢትር ብሩክ የማነብርሀን
የጨዋታ ቦታ: ትግራይ ስታድየም

ሁለት ተከታታይ ጨዋታዎች ላይ ሽንፈት ያስተናገዱት መቐለ 70 እንደርታዎች ባሳለፍነው ሳምንት ጅማ አባጅፋርን በጠባብ የግብ ልዩነት ያሸነፋትን ሀዋሳ ከተማዎችን ያስተናግዳሉ።

ባለፋት ሁለት ጨዋታዎች ያሬድ ከበደ እና ዮናስ ገረመውን በጉዳት ማጣታቸውን ተከትሎ መሀል ሜዳ ላይ የቡድናቸውን ሚዛን ያጡት አሰልጣኝ ገብረመድህን ሀይለ ከሁለቱ ተጨዋቾች ቢያንስ አንዱን ለነገው ጨዋታ ማግኘታቸው ለአሰልጣኙ እፎይታ ነው።ቀጥተኛ የሆነ አጨዋወትን ሚከተሉት መቐለዎች በነገው ጨዋታ ተጋጣሚያቸው ሀዋሳ ከተማዎች ወደ ኃላ አፈግፍገው በጥብቅ የመከላከል ስልት ሊገቡ ስለሚችሉ እነሱን ለማስከፈት ከመስመር ከሚነሱ ቀጥተኛ አጨዋወት በተጨማሪ ኳሱን በማንሸራሸር ክፍተቶችን በትዕግስት መፈለግ ሚያስፈልጋቸው ይሆናል።

መቐለ 70 እንደርታዎች ያሬድ ከበደን ከጉዳት መልስ በኃላ ሲያገኙ የአማካያቸው ዮናስ ገረመው መግባት አለመግባት በመጨረሻው ሰዐት ሚወሰን ይሆናል።በተጨማሪ ምዐም አናብስቶቹ ከፋሲል ከተማ ጋር በነበረው ጨዋታ ቀይ ካርድ የተመለከተውን ዳንኤል ደምሱን በቅጣት ሚኪኤለ ደስታን በረጅም ጊዜ ጉዳት ለነገው ጨዋታ ማያገኙ ይሆናል።

በአዲሴ ካሳ እየተመሩ 19 ነጥቦችን ሰብስበው 6ተኛ ደረጃ ላይ የተቀመጡት ሀዋሳ ከተማዎች አብዛኞቹ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ቡድኖች ከሜዳቸው ውጪ ሲጫወቱ ሚጠቀሙበትን የመልሶ ማጥቃት አጨዋወትን ይዘው ሊገቡ እንደሚችሉ ይገመታል።ከመሀል ሜዳ ዘላለም ኢሳያስ እና ኄኖክ ድልቢ በሚልክዋቸው ሰንጣቂ ኳሶች እድሎችን ሚፈጥሩት ሀይቆቹ በነገው ጨዋታም ወደ መሀል ሜዳ ተጠግተው ሊከላከሉ እንደሚችሉ ሚገመቱትን የመቐለ ተከላካይ ክፍልን ከኃላቸው ሰንጣቂ ኳሶችን በመጣል የግብ እድሎችን ለመፍጠር አቅደው ይገባሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ሀዋሳ ከተማዎች ኳስቆጠርዋቸው 14 ግቦች ግማሹን ማስቆጠር የቻለው ወጣቱ አጥቂ ብሩክ በየነ ከግራ መስመር እየተነሳ ሚያደርጋቸው እንቅስቃሴዎች በሀይቆቹ የማጥቃት እንቅስቃሴ ላይ ከፍተኛ ድርሻ ሚኖራቸው ይሆናል።

ሀይቆቹ መስፍን ታፈሰ፣እስራኤል እሸቱ እና ኄኖክ አየለ በጉዳት ምክንያት አያሰልፋም።

የሁለቱ ቡድኖች ወቅታዊ ቁጥሮች

መቐለ 70 እንደርታዎች ባለፋት ሁለት ጨዋታዎች ላይ አንድም ግብ ማስቆጠር ያልቻሉ ሲሆን በአንፃሩ 3 ግቦችን አስተናግደዋል።

ሀይቆቹ ባጠቃላይ ከሜዳቸው ውጪ 6 ጨዋታዎችን አድርገው 11 ግቦችን ሲያስተናግዱ በመጨረሻዎች ሁለት የሜዳቸው ውጪ ጨዋታዎች 5 ግቦችን ሲያስተናግዱ ማስቆጠር የቻሉት ግን 1 ግብ ብቻ ነው።

Hatricksport website writer

Twitter

ዳዊት ብርሀነ

Hatricksport website writer