የጨዋታ ቅድመ- እይታ | ሀዋሳ ከተማ ከ ፋሲል ከነማ

የመጀመሪያ ዙር የመጨረሻ ሳምንት ላይ የደረሰው የኢትዮጵያያ ፕሪምየር ሊግ ከአርብ ጀምሮ እየተካሄደ ይገኛል።እኛም የሊጉን የ15ኛ ሳምንት የመጨረሻ ጨዋታ ሀዋሳ ላይ ሀዋሳ ከተማ ከ ፋሲል ከነማ የሚያደርጉትን ቀድመን እንዲ ተመልክተነዋል።

ጨዋታ: ሀዋሳ ከተማ – ፋሲል ከነማ
የጨዋታው ቀን: እሁድ የካቲት 15/6/2012
የጨዋታው ሰአት: 9:00
የጨዋታው አርቢትር: ባምላክ ተሰማ
የጨዋታው ቦታ:ሀዋሳ ሰው ሰራሽ ሜዳ

በ14ኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ወደ ትግራይ አቅንቶ በመቐለ 70 እንድርታ በ 5-1 ሰፊ ውጤት ተሸንፈው የተመለሱት ሀዋሳ ከተማዎች በሜዳቸው ቅዱሱ ጊዮርጊስን አስተናግደው 2-2 በሆነ ውጤት ነጥብ ተጋርተው የወጡትን ፋሲል ከነማን በሜዳው ያስተናግዳል።

 

ወጥ አቋም የማይታይባቸው የአሰልጣኝ አዲሴ ካሳ ቡድን በቀደሙት ጨዋታ ቀጥተኛ ኳሶች መስርቶ የመጫወት እና በወጣቱ ብሩክ በየነ እየታገዙ የግብ እድሎችን የመፈጠር እና ባብዛኛው በሜዳው በማሸነፍ አብዛኛውን ነጥብ መሰብሰብ በሊጉ በ19 ነጥብ 7 ደረጃ ላይ የሚገኙት ሀይቆቹ በነገው ጨዋታ ከአፄዎቹ ነጥብ ለማግኘት እና ደረጃቸውን ለማሻሻል ከባድ የቤት ስራ የሚጠብቃቸው ይሆናል።

 

ከመሪው በ1 ነጥብ ዝቅ ብለው የሚገኙት እና ከፍተኛ መነቃቃት ውስጥ የሚገኙት የአሰልጣኝ ስዩም ከበደ ቡድን በነገውም ጨዋታ በተለይ በመሀል ሜዳ ኳስ በማደራጀት ከሱራፌል ዳኛቸው የሚነሱ ኳሶች የሀይቆቹ ደጅ በሊጉ ከፍተኛ ጎል አስቆጣሪ ሙጅብ ቃሲም የሚያስጨንቃቸው ይሆናል።

 

በሀዋሳ በኩል አለልኝ አዘነ በመቐለው ጨዋታ ላይ ቀይ ካርድ በመመልከቱ በነገው ጨዋታ ቡድኑን የማያገለግል ሲሆን የወሳኝ አጥቂያቸውም መስፍን ታፈሰ እንዲሁም በተከታታይ ጨዋታዎች ጉዳት ላይ የሚገኘው እስራኤል እሸቱ መሰለፋቸው አጠራጣሪ ነው።

ፋሲሎች ቅዱስ ጊዮርጊስን ባስተናገዱበት ጨዋታ ቀይ ካርድ የተመለከተው ሽመክት ጉግሳ : ኦሴይ ማውሊ እና ጀማል ጣሰው ከቡድኑ ውጪ ሲሆኑ ባንፃሩ አብድርሀማን ሙባረክ እና ሀብታሙ ተከስተ ከጉዳት የተመለሱ ናቸው።

ሁለቱ ቡድኖች እስካሁን በሊጉ ስድስት ያህል ጊዜ እርስ በእርስ ግንኙነታቸው ሀዋሳ ከተማ 2 ጊዜ ሲረታ ፋሲል ከተማ አንዱን ብቻ ማሸነፍ ችሏል። ቀሪዎቹን ሶስት ጨዋታዎች በአቻ ውጤት አጠናቀዋል።