የጨዋታ ቅድመ – እይታ | ሀዋሳ ከተማ ከ ሀድያ ሆሳዕና

 

የ 17ኛው ሳምንት ጨዋታዎች ዛሬ በተካሄደ ጨዋታዎች ሲጀመር በነገው እለት ሀዋሳ ከተማ ከ ሀድያ ሆሳዕና በደቡብ ደርቢ የሚያገናኘው መርሀ ግብር ተጠባቂው ነው ::

ይህን ተጠባቂ ጨዋታ ኢንተርናሽናል አርቢትር በአምላክ ተሰማ በበላይነት ሲመረዋ የሜዳ ላይ እንቅስቅሴው ከወዲሁ በስፖርት አፍቃሪው ይጠበቃል ::

ሀዋሳ ከተማ በሁለተኛው ዙር የመጀመሪያ ጨዋታ ሽንፈትን ሲያስተናግዱ በነገው ጨዋታ ከሽንፈት የሚያገግሙበት ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል ::

ሀዋሳ ከተማዎች በተለይም በሜዳቸው በሚያደርጎቸው ጨዋታዎች ላይ ፈጣን እንቅስቃሴን ከጥሩ የጨዋታ ፍሰት ጋር ሲያሳዩ በተለይም በማጥቃት እንቅስቃሴ ወቅት የመስፍን ታፈሰ እና የብሩክ በየነ ፈጣን እንቅስቃሴዎች ለተከላካዮችን ትልቅ ራስ ምታት ሲሆን ይስተዋላል ::

ሀድያ ሆሳዕናዎች በአዲሱ አሰልጣኛቸው ፀጋዬ ኪዳነ ማርያም እየተመሩ ባደጉበት አመት ላይ የመውረድ አደጋ ተጋርጦባቸው ሲስተዋል በሁለተኛው ዙር የመጀመሪያ ጨዋታ በመቀለ 70 እንደርታ በሜዳቸው ሽንፈትን ለማስተናገድ ተገደዋል ::

በተለይም ቡድኑ ከሜዳው ውጪ ሲጫወት የተነሳሽንነት እና የቡድኑን ስነ ልቦና ከፍ የሚያደርግ ተጫዋች ጎሎት ለመመልከት ችለናል ::

በዝውውር መስኮት የነቃ ተሳትፎን ያደረጉት ሀድያዎች ከጨዋታ ጨዋታ ማሻሻሎችን ያሳያሉ ተብሎ ሲጠበቅ የአዳዲስ ተጫዋቾቻቸው ጥምረት በጨዋታ ላይ ይጠበቃል ::

የፊት መስመራቸው ባለፉት ጨዋታዎች ላይ ተዳክሞ መታየት በመሳይ ፓውሎስ ለሚመራው የሀዋሳ ከተማ የተከላካይ ክፍል ቀላል ሆኖ ሊያልፍ ሲችል የሀድያ ሆሳዕና የተከላካይ ክፍል በሌላ በኩል በታዳጊዎቹ መስፍን ታፈሰ እና ብሩክ በየነ እንደሚፈተን ይጠበቃል ::

በሀዲያ ሆሳዕና በኩል አብዱልሰመድ አሊ በጉዳት የነገው ጨዋታ ሲያልፈው በሀዋሳ ከተማ በኩል አለልኝ አዘን በቅጣት እስራኤል እሸቱን በጉዳት  እማያገኘ ይሆናል ።

በጨዋታው ባለ ሜዳዎቹ ሀዋሳ ከተማዎች ድል የሚያደርጉ ከሆነ በደረጃው ሰንጠረዥ ወደ ስድስተኛ ከፍ ማለት ሲችል በሌላ በኩል ሀድያዎች ወሳኙን ሶስት ነጥብ ካሳኩ ነጥባቸውን በወራጅ ቀጠናው ከሚገኙት ክለቦች ወልዋሎ እና ጅማ አባ ጅፋር ጋር በነጥብ የሚቀራረቡ ይሆናል ::

Hatricksport website Editor

Twitter

kidus Yoftahe

Hatricksport website Editor