መነሻ ገጽ ሀትሪክ ስፖርትጋዜጣ የጋዜጠኛ መሸሻ ወልዴ አጭር የህይወት ታሪክ
ሀትሪክ ስፖርትጋዜጣዜና እረፍትዜናዎች

የጋዜጠኛ መሸሻ ወልዴ አጭር የህይወት ታሪክ

አጋራ
አጋራ

ጋዜጠኛ መሸሻ ወልዴ ከእናቱ ከወ/ሮ ጌጤ ገ/ስላሴ እና ከአባቱ ሀምሳ አለቃ ወልዴ ደምበል ሚያዚያ 29/1965 ዓ.ም በአዲስ አበባ ልዩ ስሙ መርካቶ ሰባተኛ ተብሎ በሚጠራው ሰፈር ተወለደ እድሜውም ለትምህርት ሲደርስ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርቱን የፊደል ገበታ ትምህርትን በየኔታ መምራ ወ/ገብርኤል ከተማረ በኋላ የአንደኛ ደረጃውን በዳግማዊ ቴዎድሮስ ከ1ኛ እስከ 6ኛ የተማረ ሲሆን በመቀጠል ደግሞ ሰባተኛ እና ስምንተኛ ክፍልን በቀድሞው ወሰንሰገድ በአሁኑ የካቲት 23 ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተከታትሏል ከዛም በመቀጠል ለትምህርት ባለው ፍላጎት በ1986 ዓ.ም በቴክኒክና ሙያ ከተግባረእድ በመካኒካል ዘርፍ ተምሮ በዲፕሎማ ተመርቋል በተጨማሪም በጋዜጠኝነት በበርካታ አጫጭር ስልጠናዎች ሰርተፍኬት አግኝቷል ለሙያው ባደረበት ፍቅር የተነሳ የዘጠነኛ ክፍል ተማሪ እያለ የጋዜጠኝነት ስራውን በፅሁፍ መልክ መስራት እንደጀመረ የህይወት ታሪኩ ይናራልም ያወሳልም ።

በ1987 ዓ/ም ጀምሮ በደንብ ሙያውን ተቀላቅሎ ህይወቱ እስካለፈበት ቀን ድረስ ስራው እና ሙያውን በፍቅር ተወጥቷል አሻራውንም አስቀምጧል በዚሁም ለአብነት ያህል ካታንጋ ፣ሻምፒዮን ፣ማራቶን ፣፣ግሎባል ፣ካምቦሎጆ ይድነቃቸው አዲስ ስፖርት ፣ቤስት ሊግ ፣እና ሀትሪክ በተሰኙት የህትመት ውጤቶች ላይ ላቅ ያለ ስራውን አበርክቷል በሬድዮ በዛሚ 90.7፣ሀበሻ ሊግ ፣በኤፍ ኤም 96.3 (ፕላኔት ስፖርት ) ላይም ሰርቷል የኢትዮጵያ ስፖርት ጋዜጠኞች ማህበር ውስጥ ለረጅም ጊዜ በአባልነት እንዲሁም በስራ አስፈፃሚነት በማገልገል ላይ ነበር አድዋ አፍሪካ አለም አቀፍ ቶርመንት በተሰኘው ድርጅትም መስራች እና የቦርድ አመራር በመሆን አገልግሏል በመርካቶ የጤና ስፖርት ማህበር ውስጥ አባል ነበር ፡፡

ጋዜጠኛ መሸሻ ወልዴ በበጎ አድራጎት ስራዎች ተሳታፊ ለተቸገሩ ፈጥኖ ደራሽ የነበረ እና በስራዎቹ አንቱታን ብሎም ምስጋንን ያተረፈ ባለሙያ ነበር ከሙያ ባልደረባዎቹም ጋር መልካም ግንኙነት ነበረው በስራውዎቹ ደግሞ በ ከአዲስ አበባ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ሁለት ጊዜ የእውቅና ሽልማት የተበረከተለት ሲሆን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንን ጨምሮ ጋዜጠኞች የሙያ ማህበራት የቀድሞ ተጫዋቾች ደጋፊዎች በአጠቃላይ የስፖርቱ ቤተሰቦች የተሳተፉበት የምስጋና መርሀ ግብር ሀሙስ ጳጉሜ 4/2013 ዓ.ም ተደርጎለት ነበር፡፡

ጋዜጠኛ መሸሻ ወልዴ በተወለደ በ50 ዓመቱ እሁድ ጥር 21/2015 ዓ.ም በድንገት ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል፡፡ ስርዓት ቀብሩም ወደጃ ዘመዶችና የሞያ አጋሮቹ በተገኙበት በቀጨኔ ደብረሰላም ተፈፅሟል።

ለቤተሰቦቹም ለስራ ባልደረቦቹ መጽናናት ይስጥልን

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና በዝናባማው ጨዋታ በመቻል ሲረታ የጣናው ሞገድም አሸንፏል

እጅግ በከባድ ዝናብ ታጅቦ በተደረገው ጨዋታ መቻል የሊጉን መሪ ሲዳማ ቡናን 3ለ1...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሀድያ ሆሳዕና ፣ ፋሲል ከነማ እና ወላይታ ድቻ ወሳኝ ድል አግኝተዋል

በሊጉ የሳምንቱ የሁለተኛ ቀን መርሀግብር ሀዋሳ ከተማ ወደ ሊጉ መሪ የሚጠጋበትን ዕድል...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ፈረሰኞቹ በድል ሲቀጥሉ ንግድ ባንክ እና ድሬዳዋም አሸንፈዋል

ቅዱስ ጊዮርጊስ ተከታታይ ድሉን ወደ ቋቱ ሲከት ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከጨዋታ ብልጫ...

ዋልያዎቹዜናዎችየኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን

አንጋፋው አሰልጣኝ በስማቸው የእግር ኳስ ማሰልጠኛ አካዳሚ ሊገነባላቸው ነው

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የቀድሞ አሰልጣኝ ኢንስትራክተር ሰውነት ቢሻውን ለማመስገን እና ዕውቅና ለመስጠት...