የጋሽ ከማል አካዳሚ ስድስት ከ15 አመት በታች ታዳጊዎችን ለባየርን ሙኒኩ አካዳሚ አስመርጧል

 

ታላቁ አሰልጣኝ ምንም እንኳን በክለብ ደረጃ ማሰልጠን ቢያቆሙም። ለወደፊቱ ለሀገሪቱ የሚጠቅሙ ተጫዋቾችን በማፍራት ተጠምደዋል። የሚገባቸውን ክብር ያላጉኙት እኚህ አሰልጣኝ በሀገራችን ስመ ጥር የሚባሉ ተጫዋቾች አብዛኛዎቹ በእሳቸው እጅ የተሟሹ ናቸው። የሚያስገርመው ግን ለታዳጊዎች ትኩረት መሰጠት አለበት የሚሉ እና 24 ስዓት ሜሲ ቁርሱን ዶሮ  በላ ብሎ ህዝቡን ሲያደነቁሩ የሚውሉት ሚድያዎቻችን የነዚህን ታዳጊ ጨዋታ በትኩረት  አለመከታተል የሚያስገርም ነው።

ካስመረጧቸው ታዳጊዎች አንዱ ግብ ጠባቂ ሲሆን ቀሪዎቹ አምስት ልጆች በተለያየ ስፍራ የሚጫወቱ ናቸው። የነዚህ ታዳጊዎች ፓስፖርት የማውጣት ሂደት የተጀመረ ሲሆን ምናልባትም ቶሎ የሚጠናቀቅ ከሆነ ማክሰኞ ወደ ጀርመን ሊያቀኑ ይችላሉ ተብሎ ይጠበቃል። የአካዳሚው ባለቤት አሰልጣኝ ከማል አህመድ ያደረግነውን ቆይታ ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ ይዤ እመለሳለሁ።

Hatricksport website Editor

Facebook

ሚሊዮን ኃይሌ

Hatricksport website Editor