በመጣበት ዓመት የ2010 የኢትዮጵያ ፕሪሚየርሊግ ቻምፒዮን የሆነው ጅማ አባጅፋር በዘንድሮ የካፍ ቻምፒየንስ ሊግ አገራችንን ወክሎ እንደሚሳተፍ ይታወቃል።
በካፍ ቻምፒየንስ ሊግ የ2018/19 የውድድር ዘመን ጅማ አባ ጅፋር ከጅቡቲው ቴሌኮም ጋር የቅድመ ማጣርያ የመጀመርያ ጨዋታውን የፊታችን ማክሰኞ ጅቡቲ ላይ ያደርገል።
ለዚህም ይረዳው ዘንድ በክረምቱ ክለቡን የለቀቁ ተጫዋቾችን በመተካት ዝግጅቱን የጀመረው ክለቡ በአዲስ አበባ ሲቲ ካፕ በመሳተፍ ሶስተኛ ሆኖ በማጠናቀቅ የፕሪሚየር ሊጉ የመክፈቻ ጫወታ አዳማ ላይ አዳማ ከተማን 2-0 በማሸነፍ የውድድር ዓመቱን ጀምርዋል። ላለፉት ሶስት ሳምንታት ዝግጅቱን ጅማ ላይ በማድረግ የፉታችን ማክሰኞ ለሚደረገው ጨዋታ ዝግጅቱን አጠናክሮ ቀጥሏል።

ጅቡቲ የሚሄዱት መላው ስብስብ አዲስ ከበባ ላይ ያለፉትን ሶስት ቀናት ዝግጅት ሲያደርጉ የቆዩ ሲሆን ከበረኛው ዳንኤል አጃይ መጠነኛ ህመም ውጭ መላው ተጫዋቾች በሙሉ ጤንነት ላይ ይገኛሉ የሚከተሉት 18 ተጫዋቾች ወደ ጅቡቲ የሚያቀኑ ይሆናል
ግብ ጠባቂዎች፡
ዳንኤል አጄይ
ዘሪሁን ታደለ
ተከላካዮች፡
አዳማ ሲሶኮ
ዐወት ገ/ሚካኤል
ኤልያስ አታሮ
መላኩ ወልዴ
ተስፍዬ መላኩ
ያሬድ ዘውድነህ
ከድር ኸይረዲ
አማካዮች፡
አስቻለው ግርማ
ይሁን እንደሻው
ንጋቱ ገ/ሥላሴ
ኤልያስ ማሞ
መስዑድ መሐመድ
ኄኖክ ገምቴሳ
ኤርሚያስ ኃይሉ
አጥቂዎች:
ዲዲዬ ለብሪ
ማማዱ ሴዲቤ
አሰልጣኝ ዘማርያም በዝግጅቱ ዙርያ በሰጡን አስተያየት ስለ ጅቡቲው ቡድን የተወሰኑ መረጃዎችን ለማግኘት ለመሰብሰብ እንደተሞከረና እና የጅቡቲውን ቡድን ደካማ ጎን ከመመልከት ይልቅ በጅማ አባጅፋር ጥንካሬ ዙርያ አጠንክረው እንደሚሰሩና የጅቡቲውን ቡድን አክብረው ወደ ስፍራው እንደሚጓዙ ገልፀውልናል
የጅማ አባጅፋር ስብስብም ዛሬ ረፋድ 10:00 ሰዓት ላይ ወደ ጅቡቲ የሚያቀና ይሆናል

አስተያየት ይስጡ