የድሬዳዋ ከተማ ቡድን አባላት በሌላ የበጎ ስራ ተሳትፈዋል

 

የድሬዳዋ ከተማ ቡድን አባላት የደም ልገሳ በጎ ተግባር አድርገዋል።

 

በአለማችን እንዲሁም በሀገራችን በመስፋፋት የሰው ሂይወት እየቀጠፈ የሚገኘው ኮሮና ቫይረስ ምክኒያት በሀገራችን የደም ለጋሾች ቁጥር በመቀነሱ የደም እጥረት እንዳያጋጥም የድሬዳዋ ከተማ ተጫዋቾች እና አሰልጣኞች ደም ለግሰዋል።

የዋናው ቡድን አሰልጣኞች፣ወንዶች እና የሴቶች እንዲሁም ከ20 አመት በታች የቡድኑ አባላት በደም ልገሳው ላይ መሳተፋቸውንከ የክለቡ ይፋዊ የፌስ ቡክ ገፅ ያስታወቀ ሲሆን። ድሬዳዋ ከተማ ከዚህ ቀደም ኮሮና ቫይረስን ለመከላከል የሚውል እገዛ ማድረጋቸው የሚታወስ ነው።