የወልዋሎ ስታዲም የሚገመግሙ ከፌደሬሽኑ የተላከው አብይ ኮሚቴ ዛሬ አዲግራት ገብተዋል።
በ2010 መጨረሻ ለእድሳት ተብሎ የፈረሰው ወልዋሎ ስታድየም በተለያዩ ምክንያቶች ግንባታው ሲጓተት ቆይቶ ከአንድ ዓመት ግማሽ በኃላ እድሳቱን ጨርሶ ለጨዋታ ዝግጁ ሊሆን ከጫፍ ደርሷል። የመጫወቻ ሜዳ ሳር ተከላ፣የፈሳሽ ውሀ ማስወገጃ ፣የሜዳ አጥር፣የዳኞች እና የተጨዋቾች መልበሻ ክፍል ከሞላ ጎደል ያጠናቀቀው ስታድየሙ ነገ(ቅዳሜ) አብይ ኮሚቴ ባዋቀራቸው የስታድየም ጥራት ተቆጣጣሪዎች ጉብኝት ካደረጉ በኋላ ሜዳው ጨዋታ ለማዘጋጀት ቡቁ ነው የሚል ውሳኔ ከሰጡ። በ2010 ወልዋሎ ከ ድሬዳዋ ከተማ ጋር ካደርጉት ጨዋታ በኃላ የፕሪምየር ሊግ ጨዋታዎችን ያላስተናገደው ስታድየሙ በ13ኛው ሳምንት ቢጫ ለባሾቹ እና ፈረሰኞቹ ሚያደርጉትን ጨዋታ ሊያስተናግድ እንደሚችል ይገመታል።
አስተያየት ይስጡ