መነሻ ገጽ ሀትሪክ ስፖርትጋዜጣ የእግር ኳሱ ቤተሰብ የከፋ ሐዘን ውስጥ ወድቋል ፤ በኢትዮጵያ እግር ኳስ ታሪክ የማይዘነጋ ወርቃማ ታሪክ ያለው አስግድ ተስፋዬ ድንገተኛ አማማት ብዙዎቹን አስደንግጣል
ሀትሪክ ስፖርትጋዜጣ

የእግር ኳሱ ቤተሰብ የከፋ ሐዘን ውስጥ ወድቋል ፤ በኢትዮጵያ እግር ኳስ ታሪክ የማይዘነጋ ወርቃማ ታሪክ ያለው አስግድ ተስፋዬ ድንገተኛ አማማት ብዙዎቹን አስደንግጣል

አጋራ
አጋራ

በይስሀቅ በላይ ከካናዳ ቶሮንቶ
ዜናውን የሰሙትን ሁሉ አሰደንግጧል፤የሆነውን ሁሉ አምነው ለመቀበል ተቸግረዋል፤አዎን የቀድሞው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ባለውለታ የነበረው አመለሸጋው አሰግድ ተስፋዬ ዳግም ወደ ዚህች ዓለም ላይመለስ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ማሸለቡ ግን መራራ ዕውነት ሆናል።
የጨዋታ ዘመኑን የትውልድ አገሩ ክለብ በሆነው ድሬዳዋ ኮካኮላ ክለብ በመጫወት የእግር ኳሱን ዓለም በይፋ የተቀላቀለው አስግድ ተስፋዬ አስደንጋጩ ዜና ዕረፍት የተሰማው በትናንትናው ዕለት ሲሆን ሁሌም ዘወትር ቅዳሜ እንደሚያደርገው የጤና ቡድን የእግር ኳስ ጨዋታ (ልምምድ) ካደረገ በኋላ መታጠቢያ ቤት ውስጥ እያለ በድንገት የመውደቅ አደጋ አጋጥሞት በዚህ ምክንያት ህይወቱ እንዳለፈ ነው የታወቀው።


አሰግድ በድንገት መታጠቢያ ቤት ውስጥ መውደቅን ተከትሎ የገጠመውን አደጋ ለመታደግና ህይወቱን ለማትረፍ ወደ ሀያት ሆስፒታል ቢወሰድም በዚህች ምድር እንዲኖር የተቆረጠለት ቀን በመጠናቀቁ ህይወቱን መታደግ ሳይቻል የሀገር ባለውለተኛ ው አሰግድ ተስፋዬ ትዝታውንና መልካም ስራዎቹን ብቻ ትቶልን በድንገት አሸልቧል።
በትናንትናው ዕለት በጨካኙና በክፉው ሞት በድንገት የተነጠቀው አሰግድ ተሰፋዬ በጨዋታ ዘመኑ የሶስት ኃያላን ክለቦች ማልያን ለብሶ የተጫወተ ሲሆን ለቅ.ጊዮርጊስ አምስት ዓመት፣ለመድን አምስት ዓመት እንዲሁም ለቡና ገበያ ለስድስት ዓመታት በአጠቃላይ ለ16 ዓመታት እግር ኳስን በትላልቅ ክለቦች ደረጃ በመጫወት ድንቅ የሚባልና የማይዘነጋን የእግር ኳስ ጊዜን አሳልፏል።
ጂረስ፣የደሃው አገር ሮማሪዮ በሚሉ ዋና ቅፅል ስሞች የሚጠራው አሰግድ ተስፋዬ በእግር ኳሱ ሲታወስ የሚኖርባቸው በርካታ አንፀባራቂ አጋጣሚዎች እንዳሉ የሚካድ ባይሆንም በተለይ በቀድሞ አጠራር ቡና ገበያ እያለ በአንድ ጨዋታ 5 ጎሎችን የሲሸልሱ ሴንት ሚሼልስ ላይ በኢንተርናሽናል ጨዋታ ላይ ያስቆጠራቸው ግቦች የማይዘነጉ ናቸው።
በ1990ዎቹ በተለይ በቡና ገበያ በሚያደርጋቸው ድንቅ እንቅስቃሴዎቹና በግብ አይምሬነቱ በብዙዎች ልብ ውስጥ መፈቀርንና የማይነቃነቅ ሀውልት ለመትከል የበቃው አሰግድ ተስፋዬ የጨዋታ ዘመኑ ከተጠናቀቀ በኃላም ከእግር ኳሱ ላለመራቅና በሙያው ለሀገሩ መልካም ነገር ሠርቶ ለማለፍ በማሰብ “አሰጌ ስፖርት አካዳሚ”ን በመክፈት የነገ የሀገር ተረካቢ ታዳጊዎችን እስከ ህልፈተ ህይወቱ ድረስ በማሰልጠን በእግር ኳሱ የራሱን አሻራ ለማስቀመጥ ብርቱ ጥረት ሲያደርግ ቆይቷል።
በሀገር ውስጥም በባህር ማዶ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን ያስደነገጠው የቀድሞ የእግር ኳሱ ባለውለተኛ አስግድ ተስፋዬ የቀብር ስነስርዓት በነገው ዕለት ይፈፀማል።
አሰግድ ባለ ትዳርና የአንድ ልጅ አባት ነበር።
የሀትሪክ ጋዜጣ ዝግጅት ክፍልና የሀትሪክ ስፖርት ድረ-ገፅ የሀገር ባለውለተኛ ተጫዋች በነበረው በአመለሸጋው አሰግድ ተስፋዬ ድንገተኛ ህልፈተ ህይወት የተሰማንን ጥልቅ ሀዘን በጋራ እየገለፅን አምላክ ዘላለማዊ ዕረፍትን ለእግር ኳሱ ቤተሰቦች፣ለማች ቤተሰቦች፣ለወዳጆቹና ለጋደኞቹ አምላክ መፅናናትን እንዲሰጥልን ከልብ እንመኛለን።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሀትሪክ ስፖርትጋዜጣዜና እረፍትዜናዎች

የጋዜጠኛ መሸሻ ወልዴ አጭር የህይወት ታሪክ

ጋዜጠኛ መሸሻ ወልዴ ከእናቱ ከወ/ሮ ጌጤ ገ/ስላሴ እና ከአባቱ ሀምሳ አለቃ ወልዴ...

ሀትሪክ ስፖርትጋዜጣ

ሀትሪክ አሁንም ቀጠሮ ማክበር ስልጣኔ ነው በሚለው አቋሟ ጸንታለች

ቅዳሜ ጠዋት በቀጠሮ  ቀናችን  እርስዎ ጋዜጣዋን በእጅዎ ያስገቡ እንጂ አዳዲስና ያልተሰሙ መረጃዎችን...

ሀትሪክ ስፖርትጋዜጣዜናዎች

ሀትሪክ አሁንም ቀጠሮ ማክበር ስልጣኔ ነው በሚለው አቋሟ ጸንታለች

ቅዳሜ ጠዋት በቀጠሮ  ቀናችን  እርስዎ ጋዜጣዋን በእጅዎ ያስገቡ እንጂ አዳዲስና ያልተሰሙ መረጃዎችን...