የኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ የመጀመሪያው ዙር ቁጥራዊ መረጃዎች ካለፉት ሶስት ዓመታት ጋር ሲነፃፀር 

 

የፍፁም ቅጣት ምት በሊጉ

በዘንድሮው የውድድር አመት ላይ በመጀመሪያው ዙር ላይ በፍፁም ሳጥን ውስጥ 27 ጥፋቶች ተስርተዋል ተብሎ ውሳኔዎች ተሰጥቶባቸዋል ::

በዚህም መሰረት 31 የፍፁም ቅጣት ምቶች ሲሰጡ ከ 2011 የውድድር አመት ጋር ሲተያይ ( 27 ፍ.ቅ.ም ) በአራት ዝቅ ብሎ ይገኛል ::

በራስ ላይ የተቆጠሩ ግቦች

በውድድር አመቱ በራስ ላይ የተቆጠሩ ግቦች ስድስት ብቻ ሆነው ተመዝግበዋል :: ይህ ደግሞ ካለፈው የውድድር አመት ጋር ሲተያይ ( አራት ) በሁለት ክፍ ብሎ ይገኛል ::

የማስጠንቀቂያ ካርዶች

የዘንድሮው የውድድር አመት ምንም እንካ በደጋፊዎች ዘንድ አንፃራዊ ሰላም የታየበት የውድድር አመት ሆኖ ቢያልፍም በተጫዋቾች ረገድ ግን ብዙ የማስጠንቀቂያ ካርዶች የተመዘገበበት የውድድር አጋማሽ ሆኖ አልፏል ::

453 የቢጫ ካርዶች ለተጫዋቾች ሲመዘዝ ይህም በተለይም ከ 2010 የውድድር አመት ጋር ሲነፃፃር በአስር ካርዶች በልጦ ተገኝቷል ::

በቀይ ካርዶች መስፈርት የዘንድሮው የውድድር አመት ተሽሎ ሲገኝ 11 የቀይ ካርዶች ሊመዘዙ ችለዋል :: ይህም በ 2010 የውድድር አመት ተመዝግቦ ከነበረው ጋር ሲነፃፀር ( 25 ቀይ ካርድ ) በ 14 ካርዶች አንሶ ይገኛል ::

ከ 453 የቢጫ ካርዶች ውስጥ 41 የቢጫ ካርድ በማየት ስሁል ሽረ ቀዳሚው ክለብ ሲሆን ሀድያ ሆሳዕና ( 40 ቢጫ ካርዶች ) እንዲሁም ጅማ አባ ጅፋር ( 33 የቢጫ ካርዶች) በመመልከት የመጀመሪያዎቹ ክለቦች ናቸው ::

ይህም በ 2010 የውድድር አመት አርባ ምንጭ ከሊጉ በተሰናበተበት አመት ከተመለከተው 38 የቢጫ ካርዶች በሶስት በልጦ ይገኛል::

 

የተጫዋቾች ጉልህ አስተዋፅዖ በጨዋታዎች ወቅት

በመጀመሪያው የውድድር አመት በጨዋታዎች ወቅት በአንድ ጨዋታ ላይ ብዙ ጎሎች ተሳትፎ በማድረግ ሶስት ተጫዋቾች ቀዳሚውን ስፍራ ይይዛሉ ::

ከነዚህም መካከል :-

1. አቤል ያለው :- የቅዱስ ጊዮርጊስ የፊት መስመር ተስፈኛ ተጫዋች ቡድኑ ሲዳማ ቡናን ገጥሞ ስድስት ጎሎች ሲያስቆጥር አራት ጎሎች ላይ ቀጥተኛ ተሳትፎ ማድረግ ችሏል ::

• አቤል ያለው በጨዋታው ሁለት ጎሎችን ሲያስቆጥር ሁለት ለጎል የሚሆኑ ካሶችን አመቻችቶ ማቀበል ችሏል ::

2. አዲስ ግደይ :- የሲዳማ ቡናው አምበል እና የቡድኑ ኮከብ ተጫዋች አዲስ ግደይ በመጀመሪያው ዙር የሲዳማ ጉዞ ላይ ቁልፍ ሚናን መጫወት ችሏል ::

• አዲስ ግደይ ሲዳማ በሜዳው ወልዋሎን ሲያሸንፍ አራት ጎሎችን ከመረብ ላይ ሲያሳርፍ ሁለት ጎሎችን እና ሁለት ለጎል የሚሆኑ ካሶችን አመቻችቶ ማቀበል ችሏል ::

3. ሽመክት ጉግሳ :- የፋሲል ከነማው ተጫዋች በደደቢት ቤት ያሳይ የነበርውን አስደናቂ ብቃት በፋሲል ቤት እየደገመ ይገኛል :: በተለይም ተጫዋቹ ፋሲል በሜዳው በሚያደርጋቸው ጨዋታዎች ላይ ከሌሎች የቡድን አጋሮቹ ጋር ጎልቶ መውጣት ችሏል ::

• ሸመክት ፋሲል ድሬድዋን በሜዳው አስተናግዶ አምስት ጎሎችን ሲያስቆጥር በአራት ጎሎች ላይ ሲሳተፍ ሁለት ጎሎች ሲያስቆጥር ሁለት ለጎል የሚሆኑ ካሶችን አመቻችቶ ማቀበል ችሏል ::

የግብ ጠባቂዎች ሚና በፕርሚየር ሊጉ

ካለፉት አመታት በተለየ መልኩ ለሀገር ውስጥ ግብ ጠባቂዎች የመሰለፍ እድል ቢሰጠም ያን ያህል ግን አመርቂ ነው ሊባል አይችልም ::

በሊጉ ከሚሳተፉ አስራ ስድስት ክለቦች መካከል ኢትዮጵያ ቡና ፤ ስሑል ሽረ ፤ ወላይታ ዲቻ ፤ ድሬድዋ ከተማ እና ሲዳማ ቡና ኢትዮጵያውያን ግብ ጠባቂዎችን እየተጠቀሙ የሚገኙ ክለቦች ናቸው ::

በግብ ጠባቂዎች በኩል በሀገራችን ብዙም ባልተለመደ መልኩ የቅዱስ ጊዮርጊሱ ኬንያዊው ግብ ጠባቂ ፓትሪክ ማታሲ በሲዳማ ቡናው ጨዋታ ላይ አቤል ያለው ላስቆጠረው ጎል አመቻችቶ ማቀበል የቻለ የመጀመሪያው ግብ ጠባቂ ነው ::

• የውጭ ሀገር ተጫዋቾች

በፕርሚየር ሊጉ 47 የውጭ ሀገር ተጫዋቾች እንደሚገኙ ይታወቃል :: በፕርሚየር ሊጉ የውጭ ሀገር ተጫዋቾችን መጠቀም እንደ ባህል እየተቆጠረ ሲመጣ በሜዳ ላይ የሚታዩ እንቅስቃሴዎች ግን በአብዛኛው ለክለቡ ብሎም ለተመልካች የማይመጥኑ ሆኖ መመልከት እየተለመደ መጥቷል ::

ለዚህ ማሳያ የሚሆነው ደግሞ ክለቦች ረብጣ ገንዘብ አውጥተው ካዘዋወራቸው በሃላ ምንም የመጫወቻ እድልን ሳያገኙ አንድ አንድ ተጫዋቾች ደግሞ ጥቂት የመጫወቻ ጊዜን አግኝተው የዝውውር መስኮቱ ሳይከፍት በስምምነት ከክለቦች ጋር ሲለያዩ ለመመልከት ችለናል ::

በአጥቂ ስፍራ ላይ ከሚጫወቱ የሊጉ የውጭ ሀገር ተጫዋቾች በሊጉ የኮከብ ግብ አግቢነት ውስጥ መግባት የቻሉት ሁለት ተጫዋቾች ብቻ ናቸው ::

የመቀለ 70 እንደርታው ናይጄሪያዊው ኦኪኪ አፎላቢ ( 6 ጎሎች ) እንዲሁም እንዲሁም የባህርዳር ከተማው ማማዱ ሲዲቤ ( 4 ጎሎች ) ብቻ ናቸው ::

• የኮከብ ግብ አግቢነት ፉክክር

ካለፉት አመታት የሊጉ ፉክክሮች የተሻለ የጎል መጠን የታየበት የ 2012 የውድድር አመት ከወዲሁ መገመት ቢያዳግትም ከወትሮው በተለየ መልኩ የኮከብ ግብ አግቢነቱ የሙጂብ ቃሲም ይመስላል ::

የፋሲል ከነማው የፊት መስመር አጥቂ በአስራ አምስት የሊጉ መርሀ ግብሮች ላይ አስራ አራት ጎሎችን ሲያስቆጥር ይህም ካለፉት ሁለት አመታት የተሻለ ሆኖ ተገኝቷል ::

በባለፈው የውድድር አመት በመጀመሪያው ዙር የመከላከያው ምንይሉ ወንድሙ እና የመቀለ 70 እንደርታው አማኑኤል ገብረ ሚካኤል በአስራ አንድ ጎሎች ሲፋጠጡ በ 2010 የውድድር አመት ላይ ጌታነህ ከበደ በዘጠኝ ጎሎች በመምራት የመጀመሪያውን ዙር ማጠናቀቅ ችሏል ::

Hatricksport website Editor

Twitter

kidus Yoftahe

Hatricksport website Editor