የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የመጀመሪያው ዙር በቁጥራዊ መረጃ ሲዳሰስ

 

በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ በመጀመሪያው ዙር የነበሩ ቁጥራዊ መረጃዎች ምን ይመስላል የሚለውን አንስተንላቹሀል።

በመጀመሪያው ዙር በጠቅላላ 120 ጨዋታዎች ሲደረጉ 69 ማሸናነፍ ሲያልቁ 19 በመሸነፍ 32 ደግሞ በአቻ ውጤት አልቀዋል። በነዚህ ጨዋታዎች በጠቅላላ 280 ጎሎች ተቆጥረዋል።

 

በመጀመሪያው ዙር 27 ዳኞች በዋና ዳኝነት ጨዋታዎችን ሲመሩ 39 ረዳት ዳኞችም ተሳትፈውበታል። 29 የጨዋታ ታዛቢዎች (ኮሚሽነር) ጨዋታዎችን ታዝበዋል።

 

በዚህ ዙር በፕሪምየር ሊጉ 392 ኢትዮጵያውያን ተጫዋቾች ሲሆኑ፤47 የውጭ ተጫዋቾች ነበሩ። ከ47 የውጭ ተጫዋቾች መሀከል 11 ግብ ጠባቂዎች ናቸው።

ኢትዮጵያ ቡና እና ወላይታ ድቻ ብቻ የውጭ ተጫዋቾች የሌሉባቸው ቡድኖች ሲሆን። ወላይታ ድቻ፣ድሬዳዋ ከተማ፣ሲዳማ ቡና፣ ስሁል ሽሬ እና ኢትዮጵያ ቡና ደግሞ ኢትዮጵያውያን ግብ ጠባቂዎች ብቻ የሚጠቀሙ ቡድኖች ናቸው።

 

አብዛኛዎች ግቦች የተቆጠሩት የተቆጠሩት በመጨረሻዎቹ 15 ደቂቃዎች ሲሆን። 1,250,000 ተመልካቾች ሊጉን ተመልክተውታል ተብሎም ይገመታል።

Hatricksport website Editor

Facebook

ሚሊዮን ኃይሌ

Hatricksport website Editor