የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ በመጀመሪያ ዙር የነበሩ ክስተቶች (ክፍል አንድ)

👉👉ቆራጥ እና አፋጣኝ የፌደሬሽኑ ውሳኔ

👉👉በሜዳ ችግር ምክንያት ከሜዳቸው ውጭ የተገደዱት ክለቦች

👉👉 የኢትዮጵያን እግር ኳስ ያጣጣለው ሀሪሰተን ሄሱ

👉👉ኤልያስ ማሞ እና እዮብ አለማየሁ

👉👉 ታሪክ ሰሪው ሙጂብ ቃሲም

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ በመጀመሪያ ዙር የነበሩ ክስተቶች (ክፍል አንድ)


ቆራጥ እና አፋጣኝ የፌደሬሽኑ ውሳኔ

ፈደሬሽኑ በዚህ ውድድር አመት ለሚፈጠሩ ችግሮች አፋጣኝ መልሸ በመስጠት ለስፖርታዊ ጭዋነት መከበር ጉልህ ሚና ነበረው። ለምሳሌ የሀድያ ደጋፊዎች ባደረጉት አላስፈላጊ ተግባር ከሜዳቸው ውጭ ከሜዳቸው ውጭ እንዲጫወቱ ቅጣት ያስተላለፈባቸው ጉዳይ ማሳያ ሲሆን። ይህ አፋጣኝ ምላሽ ይበል የሚያሰኝ ጉዳይ ነው። ደሞዝ ያልተከፈላቸው ተጫዋቾች ባቀረቡት አቤቱታ መሰረት ውሳኔውን መርምሮ ፍርዱ ይህ ብሎ የሚያሳውቅበት መንገድ በዚህ አመት በስፋት የተመለከትነው ፌደሬሽኑ ምስጋና ሊቻረው ይገባል።


በሜዳ ችግር ምክንያት ከሜዳቸው ውጭ እንዲጫወቱ የተገደዱት ክለቦች

ሜዳቸው ለፕሪምየር ሊግ ብቁ ካለመሆኑ ጋር ተያይዞ ወልዋሎ አዲግራች ዩንቨርሲቲ፣ስሑል ሽረ፣ወልቂጤ ከተማ፣ሀድያ ሆሳዕና እና ሰበታ ከተማ ሜዳቸውን አስተካክለው በፌደሬሽኑ ብቁ ነው እስኪባል ድረስ ከሜዳቸው ውጭ የተጫወቱ እና በመጫወት ላይ የሚገኙ ክለቦች ናቸው። ፌደሬሽኑ ከሚወቀሰበት አንዱ ለመጫወቻ ምቹ ያልሆነ ሜዳዎችን የሊጉ ጨዋታዎችን እንዲያካሂድ ይፈቅዳል ሲባል የነበረ ሲሆን በዚህ አምት የዚህ ችግር መቅረፍ ችለዋል።


የኢትዮጵያን እግር ኳስ ያጣጣለው ግብ ጠባቂ

በ10ኛው ሳምንት ባህርዳር ከተማ ወደ አዲስ አበባ አቅንቶ ቅዱስ ጊዮርጊስን ገጥሞ 1-0 በተሸነፈበት ጨዋታ። ሀሪስተን ሄሱ አሟሙቀው ወደ መልበሻ ክፍል ካመራ በኋላ ከእለቱ ጨዋታ አርቢትር ቴዎድሮስ ምትኩ እሰጣ ገባ ውስጥ በመግባቱ ከጫዋታ በፊት በቀይ ካርድ እንዳሰናበቱት የሚተወስ ነው። ይህ በፕሪምየር ሊጉ ታሪክ ፈጣኑ ካርድ ሲሆን። የተመዘገበው ደግሞ አሁን በተጠናቀቀው የመጀመሪው ዙር የውድድር አመት ላይ ነው። ሀሪሰተን በዋነኝነት ለምን ቀይ ካርድ ተመዘዘበት ስንል የጠየቅነው ጥያቄ የለበሰውን ማሊያ እንዲቀይር ቢነገሩው ያረኩት ማሊያ ለኢትዮጵያ እግር ኳስ በቂው ነው ( this is enough for ethiopian foot ball) ብሎ በመናገሩ እና አፀያፊ ስድብ መሳደቡ ምክንያት ነውም ብለዋል።


ኤልያስ ማሞ እና እዮብ አለማየሁ

የ2012 የውድድር ዘመን የመክፈቻ ጨዋታ ላይ ኤልያስ ማም ሀዋሳ ላይ የመጀመሪያው ግብ አስቆጣሪ ሲሆን። እዮብ አለማየሁ 48ኛ ሰከንድ ላይ ድሬዳዋ ላይ ያስቆጠራት የሊጉ ፈጣን ግብ ናት።


ታሪክ ሰሪው ሙጂብ ቃሲም

የፋሲል ከተማው አጥቂ ሙጂብ ቃሲም በ15 ጨዋታዎች 14 ግብ ያስቆጠረ በታሪክ ብቸኛው የሊጉ ተጫዋች ሲሆን። ይህን ያደረገው በዚህ የመጀመሪያ ዙር የውድድር መርሀ ግብር ነው። አጥቂው ግብ ማምረቱን አጠናክሮ የሚቀጥል ከሆነ ምናልባትም በ25 ግቦች በጌታነህ ከበደ የተያዘው የሊጉ ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪነት ሪከርድ ሊሰብረው ይችላል።

Hatricksport website Editor

Facebook

ሚሊዮን ኃይሌ

Hatricksport website Editor