የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን 2ኛውን የወዳጅነት ጨዋታ ዛሬ ያከናዉናል

ረፋድ በ5 ሰዓት የሚደረገዉ የኢትዮጵያ እና እስራኤል የወዳጅነት ጨዋታ እንደ መጀመሪያው ሁሉ የቀጥታ ሽፋን የሚኖረዉ ይሆናል።

እንደሚታወቀው ማክሰኞ ዕለት በተካሄደው የሁለቱ ሀገራት የወዳጅነት ጨዋታ 0-0 በሆነ አቻ ውጤት መጠናቀቁ ይታወሳል።

ኢትዮጵያ እና አስራኤል ከ51 አመታት በኃላ ዳግም በወዳጅነት ጨዋታ የተገናኙ ሲሆን። ከዚህ ቀደም ለመጀመሪያ ጊዜ ኢትዮጵያ ከእስራኤል በአለም ዋንጫ ማጣሪያ እ.ኤ.አ. በ1961 ዓ.ም ተጫውተው በድምር ውጤት እስራኤል 4 ለ 2 አሸንፋለች።
ከዚያም በኃላም ሶስት ጊዜ የወዳጅነት ጨዋታ አድረገዋል።
እ.ኤ.አ. 1962 ባደረጉት ጨዋታ እስራኤል 3 ለ 0 ኢትዮጵያን አሸንፋለች። እ.ኤ.አ. በ1970 ባደረጉት ሁለት የወዳጅነት ጨዋታ የመጀመሪያውን እስራኤል ኢትዮጵያ 5 ለ 1 ሁለተኛውን ደግሞ 1 ለ 1 በአቻ ውጤት ነበር የፈፀሙት።

ዛሬ ረፋድም 2ኛዉን የወዳጅነት ጨዋታ ከእስራኤል ብሔራዊ ቡድን ጋር በሪዞን ሌዞን  ባርፊልድ ስታዲየም የሚያደርግ ይሆናል።

Writer at Hatricksport

Facebook

Ermias Misganaw

Writer at Hatricksport