ወደ 2014 ቤትኪንግ ፕሪሚየር ሊግ ለማደግ የሚደረገዉ ውድድር ነገ በሀዋሳ ድልድሉ ይወጣል

በቀጣይ ዓመት የትግራይ ክልል ክለቦች በሊጉ የማይሳተፉ ከሆነ እነሱን ለመተካት የሚደረገው የስድስት ክለቦች ውድድር ከዓርብ ጀምሮ ይከናወናል።

ዘንድሮ ከሊጉ የወረዱት ሦስት ክለቦች ወልቂጤ ከተማ፣ ጅማ አባጅፋር እና አዳማ ከተማ እና ከከፍተኛ ሊግ ሦስት ምድቦች ሁለተኛ የወጡት ክለቦች ኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከ፣ ሀምበሪቾ ዱራሜ እና ኢትዮ ኤሌክትሪክ ከአርብ ጀምሮ ዉድድራቸዉን የሚጀምሩ ይሆናል።

ከሰኔ 18 እስከ ሐምሌ 4 ድረስ በሚደረገዉ ውድድርም በቀን ሦስት ጨዋታዎች የሚከወኑበት ይሆናል ። የውድድሩ የእጣ ማውጣት ሥነ-ስርዓትም ነገ ከሰዓት በሀዋሳ ተሳታፊ ክለቦቹ ባሉበት የሚወጣ ይሆናል።

@Hatricksport

Writer at Hatricksport

Facebook

Ermias Misganaw

Writer at Hatricksport