የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ለኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ድንገተኛ ሁኔታ ዝግጅት ለመከላከል የ 3,000,000 (ሶስት ሚሊየን ብር) ድጋፍ አደረገ

የሃብት ማሰባሰብ ንዑስ ኮሚቴ ሰብሳቢ አምባሳደር ምስጋነው አረዳ በፅ/ቤቱ ተገኝተው የገንዘብ ድጋፉን ተረክበዋል።

የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዝደንት ዶ/ር አሸብር ወልደጊዮርጊስ ሚኒስትሩን አምባሳደር ምስጋናውን በኦሊምፒክ ቢሮ ተገኝተው ድጋፉን በመረከባቸው አመስግነው በዚህ በሀገራችን እና በአለም ላይ የደረሰውን ወረርሽኝ መንግስታችን ለመቋቋም እና ለህዝባችን ያልተቋረጠ ድጋፍ ለማድረግ በሚያደርገው ጥረት ውስጥ የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ የበኩሉን ድራሻ ማድረግ አለበት የሚል እምነት አለን ።
በዚህም መሰረት የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ የቦርድ አባላት ያለምንም ልዩነት የመጀመሪያውን ድጋፍ 3 ሚሊየን ብር ለማድረግ ወስኗል ።


በመቀጠልም ከመንግስትና ከህዝብ ሳይለይ በተከታታይነት የሚደግፍ መሆኑን ለመግለፅ እወዳለሁ ብለዋል
የሃብት ማሰባሰብ ንዑስ ኮሚቴ ሰብሳቢው አምባሳደር ምስጋነው አረዳ በበኩላቸው በመጀመሪያ ሃገራዊ ጥሪ በክቡር ጠ/ሚ ይፋ የተደረገው
የኮቪድ-19 አገርአቀፍ ድጋፍ በተጠየቀው መሰረት አፋጣኝ ምላሽ በመስጠታችሁ እጅግ አድርገን እናመሰግናለን ።
እንደምታውቁት ይሄ ጉዳይ የብሄራዊ ደህንነት ስጋት ነው። የዜጎች አጠቃላይ የሀገር ደህንነት ነው እየሆነ የመጣው እንዳያችሁት በተለያዩ የበአለም ክፍሎች ላይ ዜጎች ምን ያህል ከስራ እየተፈናቀሉ የማምረቻ ኢንደስትሪዎች እየተዘጉ ኢኪኖሚው እየተጎዳ እንዳለ የዜጎች የመኖር ዋስትና አደጋ ውስጥ እንደወደቀ ይታያል ።
እና እኛም እንደ ሀገር በዚህ ጊዜ በጋራ ቆመን ይሄንን ጊዜ ማሳለፍ ካልቻልን ጥሎት የሚያልፈው ጠባሳ ከፍተኛ ሊሆን ይችላል እና መንግስት ይሄ ከመሆኑ በፊት በሃገራችን የቅድመ ዝግጅት መደረግ አለበት ተብሎ በርካታ ስራዎች እየተሰሩ ነው።
መንግስት ሃላፊነቱንም በሚገባ እየተወጣ ነው ።
እንደዚሁም መንግስት ብቻውን የሚያደርገው ሳይሆን ዜጎች እየአንድ አንዱ የህብረተሰብ ክፍል መሳተፍ አለበት።
ድጋፍ ማድረግ አለበት።ይህንን ማለፍ የምንችለው ብሄራዊ አንድነታችን አብሮነታችንን አጠናክረን በጋራ ቆመን ስናልፈው ብቻ ነው ።


የኦሊምፒክ ኮሚቴ ይሄንን ተረድታችሁ ሃላፊነታችሁን የብሄራዊ ጥሪን ተቀብላችሁ ድጋፍ ማድረጋችሁ የሚደነቅ ነው ።
ይህ ማለት እራስን መከላከል እራስን ማዳን ነው ይህ እንግዲህ አንድ ቦታ የሚቆም አይደለም ከአንዲት የቻይና መንደር የተነሳ ወረርሽኝ አለምን በሙሉ ቀጥ አድርጓል።
እና እኛ ከዚህ ውጭ ልወንሆን አንችልም
ቅድመ ጥንቃቄ ማድፈግ አለብን።

ማህበረሰባችንን በስነልቦና እንዲሁም በዚህ ጊዜ የሚደርስበትን የኢኮኖሚያዊ ጫና ተባብረን በጋራ ካልቆምን በስተቀር እጅግ ፈታኝ ሊሆን ስለሚችል
ይሄ ድጋፋችሁ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ሙሉ እምነት አለኝ።
የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ይሄ ለሀገራችን ትልቁ Symbolic Institution ነው ኦሊምፒክ ኮሚቴው ይሄንን ተምሳሌትነታችሁን እንደወትሮው ቀድማችሁ በማሳየታችሁ እጅግ አድርገን እናመሰግናለን ድጋፋችሁ በሌሎችም ቁሳቁሶች ይሄን ኢመርጀንሲ እስኪጠናቀቅ አብራችሁን እንደምትሰሩ ተስፋ እናደርጋለን። ብሄራዊ ድጋፍ አሰባሰብ ኮሚቴው ትልቅ ምስጋና አለው ብለዋል።

Via – eoc

hatricksport team

Hatricksport team

Facebook

hatricksport team

Hatricksport team