በሰሜን አሜሪካ የኢትዮጵያውያን የባህልና የስፖርት ፌዴሬሽን የቦርድና የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት ባሳለፉት ውሳኔ መሠረት 50 ሺ ዶላር የሚያወጣ ለኮሮና ቫይረስ ህክምና የሚውሉ ቁሳቁሶችን ወደ ሃገር ቤት ለመላክ ቃል መግባቱ ይታወሳል፡፡
የፌዴሬሽኑ ፕሬዝዳንት አቶ አብይ ኑርልኛና የቦርድ አባል የሆኑት አቶ ተድላ በላይነህ ባደረሡን መረጃ መሠረት ለህክምና የሚሆኑት ቁሳቁሶቹ ወደ ሃገር ቤት መላካቸውን ገልፀዋል፡፡ ፕሬዝዳንቱ አቶ አብይ ለ’’ጋዜጠኛ ዘርዓይ እያሱ ጨምረው እንደተናገሩት ’’ቁሳቁሶቹ የፊታችን ማክሰኞ ኢትዮጵያ ሲገቡ ከጤና ሚኒስቴር ጋር ርክክብ ይደረጋል’’ ብለዋል፡፡
ፌዴሬሽኑ ከራሱ ካዝና ወጪ አድርጎ ከገዛቸው ቁሳቁሶች ባሻገር ተጨማሪ ድጋፍ ለማድረግ ከእያንዳንዱ አባል ፌዴሬሽንና ከደጋፊዎች ገንዘብ የማሰባሰብ ስራ እየተሰራ መሆኑም ታውቋል፡፡ ገንዘቡን ለማሰባሰብ እንዲያመች የሂሳብ ቁጥር መክፈቱንም ፌዴሬሽኑ ገልጧል፡፡ አቶ አብይ ባስተላለፉት መልዕክት ’’ በሌላው አለም የሚገኙ ኢትዮጵያውያን አቻ ማህበራትና ግለሰቦች ተመሳሳይ ድጋፍ በማድረግ ለወገን እንዲደርሱ ጥሪቸውን አስተላፈዋል፡፡
via- sport 52