መነሻ ገጽ ዜናዎች የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን አጠቃላይ የሊግ ውድድሮችን ሰረዘ
ዜናዎችየኢትዮጵያ አንደኛ ሊግየኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን አጠቃላይ የሊግ ውድድሮችን ሰረዘ

አጋራ
አጋራ

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ  በ2012ዓ.ም ሲካሄዱ የነበሩ አጠቃላይ የሊግ ውድድሮች  እጣ ፈንታ ላይ ዛሬ ከረፋዱ 5ሰዓት ሚያዚያ 27/2012ዓ.ም በቴሌ ኮንፍረንስ እና በአካል በፌዴሬሽኑ ጽ/ቤት ባካሄደው  አስቸኳይ ስብሰባ ሁሉም የሊግ ውድድሮች ሙሉ በሙሉ መሰረዙን አሳውቋል፡፡
በኮሮና ቫይረስ ወረርሽ ምክንያት የተቋረጡ የሊግ ውድድሮች ቀጣይ እጣ ፈንታ ላይ ውይይት ያደረገው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ከዚህ ቀደም ከመንግስት እንዲሁም ዛሬ ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አብይ ኮሚቴ ጋር በጉዳዩ ላይ  የመከረ ሲሆን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ በኮሮና ወረርሽኝ ምክንያት ሀገራችን በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ላይ ስለምትገኝ እና ወረረሽኙን እንደ ሀገር መቆጣጠር እንደሚቻል ማወቅ አሰስቸጋሪ በሆኑ በቀጣይ ጊዜያት ውድድሮችን ማካሄድ እንደማይቻል በመገንዘብ የሚከተለውን ውሳኔ ስራ አስፈጻሚው አስተላልፏል፡፡
የ2012 ሁሉም የሊግ ውድድሮች ሙሉ በሙሉ ተሰርዘዋል፤ ውድድሩ በመሰረዙም በየትኛውም ሊግ ሻምፕዮን እንዲሁም ወራጅ የሌለ በመሆኑ ቀጣይ አመት በአፍሪካ ሻንፒዮንስ ሊግ እና በኮንፌዴሬሽን ካፕ ኢትዮጵያን የሚወክል ክለብ አይኖርም፡፡ በ2012 ሰኔ 30 ኮንትራታቸው የሚጠናቀቅ ተጫዋቾች የኮንትራት ጊዜያቸው እስከሚጠናቀቅ ድረስ ክለቦች ኮንትራታቸውን እንዲያከብሩ መወሰኑን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አሳውቋል፡፡

Via -eff

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየዲሲፕሊን ውሳኔዎችዲሲፕሊን ውሳኔ

የ32ኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

የዲሲፕሊን ውሳኔዎች አህመድ ረሺድ (ድሬደዋ ከተማ) : በኢትዮጵያ ዋንጫ ውድድር 1 እንዲሁም...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሀምራዊ ለባሾቹ እና የጣና ሞገዶቹ ጣፋጭ ሦስት ነጥብን ወደ ቋታቸው ከተዋል

በሊጉ የሳምንቱ የሁለተኛ ቀን ጨዋታ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ባህርዳር ከተማ ወሳኝ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሲዳማ ቡና ሲሸነፍ በተጠባቂው ጨዋታ መቻል በጎል ፌሽታ ነገሌን ረቷል

በሳምንቱ የመጀመሪያ ቀን ጨዋታ የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና በሀድያ ሆሳዕና ሽንፈት ሲያስተናግድ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

ውጤት ለውጧል የተባለው ዳኛ ተባረረ

በዮሴፍ ከፈለኝ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውጤት ለውጠዋል የተባሉ አርቢትሮችን ወደመጡበት መመለሱን አሁንም ቀጥሏል። ከቀናት...