የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ድጋፍ ለሚስፈልጋቸው አሰልጣኞችና አንጋፋ አትሌቶች የገንዘብ ድጋፍ ለማድረግ ወሰነ

ፌዴሬሽኑ በክልልና ከተማ አስተዳደሮች ለሚገኙና ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው አትሌቶች፣ አሰልጣኞችና አንጋፋ አትሌቶች የገንዘብ ድጋፍ ለማድረግ ወሰነ።

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ረብዑ ሐምሌ 22/2012 ዓ ም ባካሄደው ስብሰባ በ9ኙ ክልሎችና በ2ቱ ከተማ አስተዳደሮች ስር ለሚገኙና ድጋፍ ለሚገባቸው አትሌቶች፣ አሰልጣኞችና አንጋፋ አትሌቶች የ3 ሚሊዮን 4 መቶ ሺ ብር ድጋፍ ለማድረግ ውሳኔ አሳልፏል።

የተወሰነውንም ገንዘብ የክልልና ከተማ አስተዳደር አትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ከስፓርት ኮሚሽኖቻቸው ጋር በመተባበር በሚላክላቸው መስፈርት መሰረት ተግባራዊ እንዲያደርጉ አቅጣጫ ተቀምጧል።

ዝርዝር ጉዳዩንና አፈፃፀሙን አስመልክቶም ፌዴሬሽኑ በሚቀጥለው ሣምንት ለስፓርት ሚድያ አካላት በፌዴሬሽኑ መሰብሰቢያ አዳራሽ ጋዜጣዊ መግለጫ ይሰጣል።

VIA- EAF

hatricksport team

Hatricksport team

Facebook

hatricksport team

Hatricksport team