የኢትዮጲያ ፕሮፌሽናል ተጨዋቾችና ባለሙያዎች ማህበር ኢንስትራክተር ሰውነት ቢሻው ላይ ተቃውሞ አቀረበ

 

አሰልጣኝ ሰውነት በቲቪ 9 ላይ በሰጡት ትንተና ተጨዋቾች ከሌላው ሙያ አይለዩም መንግስት ብር የለኝም ካለ በቃ የለውም የግድ ደመወዝ መክፈል የለበትም ማለታቸውን ማህበሩ ተቃውሞታል፡፡ እንደ ማህበሩ ቅሬታ አሰልጣኙ ትላንት በክለብና በብሄራዊ ቡድን ያሰለጠኗቸውን ተጨዋቾችና የሙያ ባልደረቦቻቸውን ከግምት ያላስገባና ቅር ያሰኘ አቋም ነው ሲል ተችቷል፡፡

የአሠልጣኙ መግለጫ የፌዴሬሽኑን አቋም የማያንጸባርቅና ክለቦችን ወደ ተሳሳተ አቅጣጫ የሚወስድ ነው በማለት ከሷቸዋል፡፡

Editor at Hatricksport

Facebook

ዮሴፍ ከፈለኝ

Editor at Hatricksport