የአፍሪካ እግር ኳስ እና ወቅታዊው ኮሮና ቫይረስ !

 

የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ከዓለም አልፎ አፍሪካ ላይ ከተጋረጠ ወራቶችን ሲያስቆጥር እግር ኳሱ ላይ የራሱን አሻራ እያሳረፈ ይገኛል ::

በርካታ የአፍሪካ ሀገራት ሊግ በገንዘቡ ረገድ ተዳክመው ሲታዪ ሀገራችን ኢትዮጵያ በዘርፉ ከሚጠቀሱ ሀገራት ተርታ ትሰለፋለች :: ይህ ወረርሽኝ ከ አስራ ሰባት ሀገራት በላይ ሊጎቻቸውን እንዲያቋርጡ ሲያስገድድ እንደ ታንዛኒያ ፣ ቡሩንዲ እና ሶማሊያ ሊጋቸውን በማካሄድ ላይ ሲገኙ ግብፅ እና ሞሮኮን ጨምሮ ጥቂት ሀገራት ሊጋቸውን ዳግም ለማካሄድ በዝግጅት ላይ ይገኛሉ ::

የምስራቅ አፍሪካዊቷ ሀገር ብሩንዲ ሊጓን በማካሄድ የዘንድሮውን የውድድር ዓመት ያጠናቀቀች ቀዳሚዋ ሀገር ለመሆን ችላለች ::

በዚህ ወረርሽኝ የሊጉ ክለቦች እና ተጫዋቾች በስፋት እየተጠቁባቸው ከሚገኙ ሀገራት ወስጥ ግብፅ እና ደቡብ አፍሪካ ዋነኞቹ ናቸው ::

ለአብነት ያክል የደቡብ አፍሪካው ሊግ በቀድሞው አጠራሩ አብሳ ፕርሚየር ሺፕ ይፋ በሆኑ እና በተረጋገጡ መረጃዎች ሁለት ተጫዋቾች መያዛቸውን ይፋ አድርገዋል ::

1. ጊቭን ማሺኪኒያ :- ብሎም ፋውንቴን ሴልቲክ ክለብ እየተጫወተ የሚገኘው የመሀል ሜዳው ተጫዋች ጊቭን ማሺኪኒያ በቫይረሱ መያዙ ከሶስት ቀናት በፊት ክለቡ ይፋ አድርጓል ::


2. ቤን ሞትሽዋሪ :- የኦርላንዶ ፓይሬትስ የመሀል ሜዳ ተጫዋች የሆነው ቤን ሞትሽዋሪ ከወራት በፊት ቫይረሱ እንዳለበት የተገለፀ ሲሆን አሁን ላይ ሙሉ ለሙሉ ማገገሙን ክለቡ በማህበራዊ ድህረገጹ አሳውቋል ::

የሰሜን አፍሪካዊቷ ሀገር ግብፅ ሊጓን ዳግም ለማካሄድ ውሳኔ ላይ መድረሳቸውን ተከትሎ የሊጉ ክለቦች የቫይረሱን ምርመራ እንዲያደርጉ ሲያስጠነቅቁ በተደረገላቸው ምርመራ ስድስት ተጫዋቾች ከአራት ክለብ መያዛቸው ይፋ ሲደረግ አራቱ ክለቦችም ሱሞሀ ፣ ( ENPPI) ፣ ኢቲሀድ አሌክሳንድሪያ እና አል ሞክዋለን መሆናቸው ተግልጿል ::

የግብፅ ሊግ መጀመሩን ከተቃወሙ ክለቦች ውስጥ ቀዳሚው የሆነው በአወዛጋቢው ፕሬዝዳንት መንሱር ማንቶርዳ የሚመራው ዛማሌክ ክለብ ሲሆን ከደቂቃዎች በፊት ግብ ጠባቂያቸው ሞሀመድ አዋድ መያዙን የግብፅ መገናኛ ብዙሃን ክለቡን ዋቢ አድርገው ዘግበዋል ::

ይፋ በሆኑ መረጃዎች ይህ ፁሁፍ እስከ ተጠናከረበት ድረስ ከአስራ ሶስት በላይ ተጫዋቾች ሲያዙ የግብፅ ሶስተኛው ዲቪዝዮን ክለብ ባድራ የ 59 አመት የግብ ጠባቂዎች አሰልጣኝ አብዶ በኮሮና ቫይረስ ህይወታቸው ማለፉ የተገለፀ ብቸኛው የስፖርቱ አለም ግለሰብ ናቸው ::

ሊጎችን ዳግም ለማስቀጠል እየተሰሩ ያሉ ስራዎች በአንዳንድ ሀገራት ቢኖሩም ካፍ በመጪው ማክሰኞ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ስብሰባ ሲያካሂድ የአፍሪካ ዋንጫን ጨምሮ በስሩ ያሉ ውድደሮች ላይ ውሳኔ እንደሚያስተላልፍ ይጠበቃል ::

Hatricksport website Editor

Twitter

kidus Yoftahe

Hatricksport website Editor