መነሻ ገጽ ዜናዎች የአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ የሚካሄድበት ቀን ታውቋል።
ዜናዎችየአዲስአበባ ከተማ ዋንጫ

የአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ የሚካሄድበት ቀን ታውቋል።

አጋራ
አጋራ

ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መጀመር በፊት ክለቦች እንደ አቋም መለኪያ የሚጠቀሙበት የአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ በአዲስ አበባ እግር ኳስ ፌደሬሽን አዘጋጅነት ለ13ኛ ጊዜ ከ ጥቅምት 3-18 2011 ድረስ እንደሚካሄድ ከአዲስ አበባ እግር ኳስ ፌደሬሽን ያገኘነው መረጃ ያስረዳል።

በዚህ ውድድር ላይም 8 ክለቦች የሚሳተፉ ሲሆን እስካሁን 7 ቡድኖች ታውቀዋል። እነሱም በ2011 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የሚሳተፉት ሶስቱ የአዲስአበባ ክለቦች ማለትም የአምናው የውድድሩ አሸናፊ ቅ/ጊዮርጊስ የአምናው የውድድሩ የዋንጫ ተፋላሚ ኢትዮጵያ ቡና እና መከላከያ ሲሆኑ በተጋባዥነት ደግሞ አምና ተጋባዥ የነበሩት አዳማ ከተማና ጅማ አባጅፋር እንዲሁም ዘንድሮ የተጋበዙት ፋሲል ከተማ እና ወላይታ ድቻ ይገኙበታል። ስምንተኛው ቡድን ከኢትዮጵያ ውጪ ከምስራቅ አፍሪካ ከሚገኝ ክለብ አንዱን ለመጋበዝ ጥረት እየተደረገ እንደሆነ እና እሱ የማይሳካ ከሆነ አምና ከፕሪሚየር ሊጉ የወረደው ከኢትዮ-ኤሌክትሪክ እና አዲስአበባ ከተማ አንዱ ሊሆን እንደሚችል ተጠቅሷል።

ሆኖም ግን ውድድሩ እንዲካሄድ የተያዘለት ቀነ ቀጠሮ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ይጀመራል ተብሎ ከታሰበበት ቀን ጥቅምት 17/2011 ጋር የሚጋጭ ሆኗል። ይህንንም ተከትሎ የአዲስአበባ እግርኳስ ፌደሬሽን እና የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ሰኞ መስከረም 7/2011 ዓ.ም ውይይት እንደሚያደርጉ ተሰምቷል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየዲሲፕሊን ውሳኔዎችዲሲፕሊን ውሳኔ

የ32ኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

የዲሲፕሊን ውሳኔዎች አህመድ ረሺድ (ድሬደዋ ከተማ) : በኢትዮጵያ ዋንጫ ውድድር 1 እንዲሁም...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሀምራዊ ለባሾቹ እና የጣና ሞገዶቹ ጣፋጭ ሦስት ነጥብን ወደ ቋታቸው ከተዋል

በሊጉ የሳምንቱ የሁለተኛ ቀን ጨዋታ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ባህርዳር ከተማ ወሳኝ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሲዳማ ቡና ሲሸነፍ በተጠባቂው ጨዋታ መቻል በጎል ፌሽታ ነገሌን ረቷል

በሳምንቱ የመጀመሪያ ቀን ጨዋታ የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና በሀድያ ሆሳዕና ሽንፈት ሲያስተናግድ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

ውጤት ለውጧል የተባለው ዳኛ ተባረረ

በዮሴፍ ከፈለኝ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውጤት ለውጠዋል የተባሉ አርቢትሮችን ወደመጡበት መመለሱን አሁንም ቀጥሏል። ከቀናት...