ባሳለፍነው ዓመት የኢትዮጵያ ፕሪሜየርሊግ ከመውረድ ለጥቂት የተረፈው ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ በ2011 ኢትዮጵያ ፕሪመየር ሊግ ተፎካካሪ ለመሆን በክረምት የተጨዋቾች ዝውውር በንቃት እየተሳተፈ ይገኛል።
እስካሁን ድረስ ስድስት ተጨዋቾችን ያስፈርመው ኣሰልጣኝ ፀጋይ ኪዳነ ማርያም በአጥቂ ክፍል ያለውን ኣማራጭ ለማብዛት ሻሂድ ባቢንቶን ፋዩ ከናይጀርያ እንዲሁም ካራንጎን ከማሊ ለሙከራ ኣምጥቷል።ናይጀርያዊው ባቢንቶን ፋዩ በ2017 ዓለም ዋንጫን ያነሳው የናይጀርያ ከ17 ዓመት በታች ቡድን ውስጥ የነበረ ሲሆን በክለብ ደረጃም ለሱማል፣ፕራይም እና ኦል ስታርስ መጫወት ችሏል። ከሁለቱም ተጨዋቾች የተሳካ ጊዜ ሚያሳልፈው አንድ ተጨዋች በቋሚነት እሚፈርም ይሆናል።
በተጨማሪም አምና አንደኛ ሊግ ላይ ከራያ አዘቦ ጋር ጥሩ ጊዜ ያሳለፈው ሰመረ ካሕሳይ ከዋና ቡድኑ ጋር እየተዘጋጀ ይገኛል።ግብ ጠባቂ በማፈላለግ ላይ ሚገኙት ወልዋሎ አዲግራቶች በቅርብ ቀን የውጭ ዜጋ ግብ ጠባቂ እንደሚያስፈርሙ ይጠበቃል።
መቐለ ላይ ቅድመ ውድድር(pre season) ዝግጅታቸውን በማድረግ ላይ ሚገኙት ወልዋሎ ዓ/ዩኒቨርሲቲ በትግራይ እግር ኳስ ፌዴሬሽን እና ሽቶ ሚድያ ትብብርነት በሚዘጋጀው ሲቲ ካፕ እንደሚሳተፋም ታውቋል።