አዲስአበባ ከተማ የአማካይ ስፍራ ተጫዋች አስፈርሟል !!

ባሳለፍነዉ የዉድድር አመት ከከፍተኛ ሊጉ ምድብ ለ የአንደኝነት ደረጃን በመያዝ ወደ ፕሪሚየር ሊጉ ማደግ የቻሉት አዲስአበባ ከተማዎች አማካዩን ዋለልኝ ገብሬ ማስፈረማቸዉ ተረጋግጧል።

በ2013 የዉድድር አመት አጋማሽ ላይ ጅማ አባጅፋርን ተቀላቅሎ የነበረዉ አማካዩ ስድስት ወራትን ቆይታ ካደረገበት ጅማ ጋር ምንም እንኳን ቀሪ የ6 ወር ኮንትራት ቢኖረውም በስምምነት በመለያየት በዛሬው ዕለት ለመዲናዉ ክለብ የአንድ አመት ዉል መፈረሙ ታዉቋል።

የአማካይ ስፍራ ተጫዋቾች የሆነው ዋለልኝ ገብሬ ጅማ አባጅፋር ከገባበት አጣብቂኝ ውስጥ ወጥቶ በሊጉ እንዲቆይ ትልቅ አስተዋጽኦ ማድረጉ ይታወሳል

Writer at Hatricksport

Facebook

Ermias Misganaw

Writer at Hatricksport

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *