የአሸናፊ በጋሻው የምስጋናና የዕውቅና መርሃግብር ተካሂዷል

 

በኢንተርኮንቲኔንታል ሆቴል ለዚህ ፕሮግራም አቶ ኢሳያስ ጅራ የኢት.እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ኢንጂነር ኃይለየሱስ ፍሰሃ የአዲስ አበባ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት መቶ አለቃ ፈቃደ ማሞ የኢትዮጲያ ቡና እግር ኳስ ክለብ ፕሬዝዳንት የቀድሞ የዋሊያዎቹ አለቃ ኢንስትራክተር አብርሃም መብራቱ እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡ አቶ ኢሳያስ እንዳሉት ” ያልተለመደ ነገር እያደረጋችሁ ነው …አሸናፊ የተጫወተው ለኢትዮጲያ ቡና ኮሚቴው ግን እነ አቶ ኢሳያስ የኤሌክትሪክ እግር ኳስ ሃላፊ ነው እነ አንዋርም ሌሎቻችሁም ጥሩ ስራ ሰርታችሁዋልና ከመሳሳብ ወጥተን ለተሻለ ስራ የሚስበንጊዜ ላይ እንዳለን አሳይቶኛልና ደስተኛ ሆኛለሁ” ሲሉ ገልጸዋል፡፡ አሸናፊ በጋሻው ለኢትዮጲያ ቡና 12 አመት ሲጫወት የማሊያው ቁጥር 12 መሆኑ ግጥምጥሞሹን የተለየ አድርጎታል፡፡ የኢት.ቡናው የቦርድ ፕሬዝዳንት መቶ አለቃ ፈቃደ ማሞ ኮሚቴውን አመስግነዋል፡፡” የአሸናፊን የቡና ተሳትፎ በዚህች ጊዜ መናገር አይቻልም ከC እስከ A ተሰልፎ ተጫውቷል የክለቡ ነብር ማለት ነው ደጋፊውን በታላቅ ወኔ ሲመራ የነበረ ተጨዋች ነው ሽንፈትን በፍጹም አይቀበልም አንድ ታሪክ ልንገራችሁ አንዴ ከምድርጦር ጋር እየተጫወትን 2ለ1 መሩን ብንሞክር ብንሞክር ግብ እንቢ አለን አሸናፊ ግን ረብሻ ፈጠረና ጨዋታው ተቋረጠ፡፡ አሰልጣኝ ስዩም አባተ ጋር ሄድኩና ለምንድነው አሸናፊ ረብሻ ያነሳው ስለው አታውቀውም እንዴ እሱኮ ሽንፈት አይወድም አለኝ ይሄ ነው አሸናፊ”በማለት አሞግሰውታል፡፡

“በአንድ ወቅት በተፈጠረ ችግር ክለባችን ደመወዝ መክፈል አልችል ሲል ሁሉም ተጨዋቾች ወደሌላ ክለብ ሲሄዱ አሸናፊ ግን ቡናን አልለቅም ቡና በችግር መመለስ ካልቻለ እኔም አልመለስም እንጂ የማንንም ደጅ አላንኳኳም ያለ ጀግናችን ነው አሸናፊ 12 ቁጥር ማሊያ ሲለብስ ኖሯል አሁንም ይህን ቁጥር ለደጋፊዎቻችን ስንሰጥ በሁሉም ልብ ውስጥ እንዳለ ርግጠኞች ነን በቀጣይም ተመሳሳይ ፕሮግራም ይኖረናል ” በማለት ፕሬዝዳንቱ አስረድተዋል፡፡ ፕሮግራሙ ቀጥሏል.. ክለቡ የደጋፊ ማህበሩ ሽልማት ሰጥተውታል፡፡ ኮሚቴውም 2 ወራት ከሰራ በኋላ የተሰበሰበውን 905 ሺ ብር ለአሸናፊ በጋሻው አበርክተውለታል፡፡

Editor at Hatricksport

Facebook

ዮሴፍ ከፈለኝ

Editor at Hatricksport