የቄራ አንበሳ እግር ኳስ ቡድን በ6 የብሄራዊ ሊግ ክለቦች መካከልና በ2 ሌሎች የውድድሩ አድማቂ ቡድኖች መሀል በአልማዝዬ ሜዳ ሲያካሄድ የነበረው የአሰልጣኝ ስዩም አባተ የመታሰቢያ ውድድር እሁድ ዕለት ፍፃሜውን አድርጎ በንፋስ ስልክ ላፍቶ እግር ኳስ ቡድንና በኢትዮጵያ ቡና የቀድሞ ቡድን አሸናፊነት ሊጠናቀቅ ችሏል።
የአገር ባለውለተኛውን እና በቅርቡ በሞት ያጣነውን አሰልጣኝ ስዩም አባተን ለማሰብ በተዘጋጀው የ6ቱ የከፍተኛ ሊግ ክለቦች ውድድር ንፋስ ስልክ የውድድሩ አሸናፊ የሆነው የልደታ እግር ኳስ ቡድንን 1ለ0 በማሸነፍ ሲሆን በሌላኛው የውድድሩ ማድመቂያና የፍፃሜ ጨዋታ ደግሞ ባለፈው ሳምንት ተደርጎ በነበረው የመክፈቻ ጨዋታ 1ለ1 በሆነ ውጤት ተለያይተው በነበሩት የቀድሞ የኢትዮጵያ ቡና ተጨዋቾች እና የቄራ አንበሳ የጤና ቡድን መካከል ድጋሚ ግጥሚያ ተደርጎ ኢትዮጵያ ቡና በካሊድ መሀመድ እና መስዑድ መሀመድ ግቦች 2ለ0 በማሸነፍ ዋንጫውን እንደ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ቡድን ሁሉ ሊያነሳ ችሏል።

አስተያየት ይስጡ