በዮሴፍ ከፈለኝ
የፊታችን ቅዳሜ ሊካሄድ ቀን የተቆረጠለት የ3ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ኘሪሜየር ሊግ ጨዋታ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ
የቡናን የተወሰኑ ደጋፊዎች ወደባህርዳር ለመውሰድ
በዝግጅት ላይ በመሆናቸው ጨዋታው እንዲራዘም
ያቀረቡት ጥያቋ ተቀባይነት አግኝቷል።
ም/ል ከንቲባው የስፖርታዊ ጨዋነት ለማስፈን እየተደረገ ያለውን ጥረት ለማገዝ ወደተለያዩ ከተሞች ደጋፊዎችን ለመውሰድና ክልላዊ ስሜትን አስወግዶ ኳሱን የሰላም መድረክ ለማድረግ የገቡትን ቃል
ወደተግባር ለመቀየር የተነሱ ሲሆን ባህርዳር የጉዞው
መጀመርያ ሆናለች።
ፌዴሬሽኑም የከንቲባውን ድጋፍ በደስታ የተቀበለው ሲሆን ሊግ ኮሚቴ አባላት ለነገ 6 ሰአት ስብሰባ መጠራታቸው ታውቋል።
ኢትዮጲያ ቡና 2ቱንም ጨዋታ ሲያሸንፍ ወልዋሎዎች
ሁለቱንም ጨዋታ ሲሸነፉ አንድም ጎል አላስቆጠሩም።2ኛ እና 16 ኛ ሆነው የሚገኙት የሁለቱ ክለቦች ጨዋታ መቼ ይካሄዳል የሚለው ነገ የሚወሰን ይሆናል።
በበርካቶች እንደሚደገፍ የሚጠበቀው የከንቲባው ጥረት እንዲሳካ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ትብብር
ይጠበቃል።