የኘሪሚየር ሊጉ የመጀመሪያው ዙር ቁጥራዊ መረጃዎች ካለፉት ሶስት ዓመታት ጋር ሲነፃፀር (ክፍል-1)

የኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ የመጀመሪያው ዙር ጨዋታዎች ሲጠናቀቁ ሀትሪክ ስፖርትም የሊጉ የመጀመሪያ ዙር ቁጥራዊ መረጃዎች እንዲሁም ካለፉት ሶስት አመታት የሊጉ ሁነቶች ጋር ሲነፃፀር ምን ይዘት ነበረው የሚለውን ወደ እናንተ ቤተሰቦቻችን በሁለት ክፍል የምናደርስ ይሆናል ::

በዘንድሮው የሊጉ የውድድር አመት ካለፉት ሶስት አመታት ጋር ሲነፃፀር የተሻለ የጎል ብዛት የታዩበት ሲሆን ለተመልካችም አዝናኝ ሆኖ ማለፍ ችሏል ::

በዘንድሮው የውድድር አመት ላይ 279 ጎሎች ከመረብ ላይ ሲያርፉ ይህም ከሶስቱ አመታት የተሻለ ቁጥር ሆኖ ተገኝቷል :: ይህንንም ተከትሎ በአማካይ በየጨዋታው 2.32% ጎሎች ሲቆጠሩ ይህም በአብዛኞቹ ጨዋታዎች ላይ የጎል ድርቅ ሳይኖር ተመልካቹ ጎሎችን በብዛት የተመለከተበት የመጀመሪያ ዙር ሆኗል ::

ከተቆጠሩት 279 ጎሎች ውስጥ በአማካይ 65% የሚሆኑት ጎሎች በባለሜዳው ቡድን ሲቆጠር የተቀረው 35% የሚሆኑት ጎሎች ደግሞ በባለጋራ ( ከሜዳቸው ውጪ ) ባሉ ተጋጣሚ ቡድኖች የተቆጠሩ ጎሎች ሆነዋል ::

ያለፉት ሁለት አመታት ማለትም የ 2010 እና 2011 የውድድር አመት በጎል ረገድ ምን ይመስላል የሚለው በምስሉ ላይ ተካተዋል ::

በምስሉ ላይ እንደተገለፀው በ 2010 የውድድር አመት 210 ጎሎች ከመረብ ላይ ማረፍ ሲችሉ ከሶስቱም የውድድር አመት አነስተኛው ሆኖ ሲመዘገብ በ 2011 የባለፈው የውድድር አመት ደግሞ 227 ጎሎች ከመረብ ላይ አርፈዋል ::

በ 2011 ከተቆጠሩት 227 ጎሎች ውስጥ አብዛኞቹ ማለትም 126 ጎሎች በባለ ሜዳው ቡድን ሲቆጠር የተቀሩት 71 ጎሎች በባለ ጋራ ቡድን ( ከሜዳቸው ውጪ ) በሚጫወቱ ቡድኖች ሊቆጠሩ ችለዋል ::

ከአጋማሾች አንፃር 

በተደረጉት 120 ጨዋታዎች በአጠቃላይ ከተቆጠሩት 279 ጎሎች ውስጥ 132ቱ ጎሎች በመጀመሪያ 147ቱ ደግሞ በሁለተኛው አጋማሽ ከመረብ ላይ አርፈዋል ።

– በመጀመሪያው አጋማሽ በፋሲል ተካልኝ የሚመራው ባህርዳር ከተማ 14 ግቦችን በማስቆጠር ቀዳሚ ሲሆን ፋሲል ከነማ ( 12 ጎሎች ) እንዲሁም ሲዳማ ቡና 11 ግቦችን በማስቆጠር ቀዳሚዎች ሶስት ክለቦች ናቸው።

– በሁለተኛው አጋማሽ ሲዳማ ቡና 17 ግቦችን በማስቆጠር ቀዳሚውን ስፍራ ሲይዙ ቅዱስ ጊዮርጊስ ( 16 ጎሎች ) እንዲሁም ፋሲል ከነማ ( 13 ጎሎች ) በማስቆጠር የመጀመሪያዎቹን ሶስት ደረጃ ይዘዋል ::

ከክለቦቹ የደረጃ ሁኔታ አንፃር በሁለተኛው አጋማሽ ያስቆጠሯቸው ጎሎች ከፍተኛ ሲሆን ይህም ውጤት እንዲያስመዘግቡ እንደረዷቸው መመልከት ይቻላል።

ስሁል ሽረ እና ሀድያ ሆሳዕና በመጀመሪያው አጋማሽ ( 5 ጎሎችን ) በማስቆጠር የመጨረሻውን ደረጃ ሲይዙ ጅማ አባ ጅፋር ደግሞ በሁለተኛው አጋምሽ ( 3 ጎሎችን ) ብቻ በማስቆጠር በትንሽ ግብ የመጨረሻውን ደረጃ ይይዛል ::

የጨዋታ ውጤቶች በቁጥራዊ መረጃ

ካለፉት አመታት በተሻለ መልኩ ከላይ እንደተገለፀው ጎሎችን ስንመለከት የዘንድሮውን የውድድር አመት ለየት የሚያደርገው ያለ ጎል የተጠናቀቁ ጨዋታዎች አነስተኛ መሆን ነው ::

በዘንድሮው የመጀመሪያው ዙር የውድድር አመት ላይ 17 ጨዋታዎች ላይ ብቻ የ 0-0 ውጤቶችን ለመመልከት ችለናል ::

ይህም ካለፈው የ 2011 የውድድር አመት ጋር ሲተያይ (21 ጨዋታዎች ) በአራት ጨዋታዎች ዝቅ ብሎ ይገኛል ::

ከአቻ ውጤቶች በተጨማሪ ከስር በምስሉ ላይ ሊገለፅ እንደተሞከረው በዘንድሮው የውድድር አመት በ 31 ጨዋታዎች ላይ የ 1-0 ውጤቶች ሲመዘገቡ በ 15 ጨዋታዎች ላይ ደግሞ የ 2 – 1 ውጤቶች ሊመዘገቡ ችለዋል ::

 

የክለቦች ወጥ አቋም ባለፉት ሶስት አመታት

የፕርሚየር ሊጉ ክለቦች በሶስት አመታት ውስጥ የተለያዩ ውጤቶችን ሊያሳዩ ችለዋል ::

ባለፉት ሶስት አመታት የሊጉ ጉዞ ላይ ቀጣይነት ያለው ወጥ ጉዞ ያደረጉ ክለቦችን መመልከት እምብዛም አልታየም ::

 

በውድድር አመቱ ላይ ክለቦች በተለይም ወጥ ላልሆነ የሜዳ ላይ እንቅስቃሴዎች ክለቦች በውድድሩ አጋማሽ ላይ የሚያጋጥማቸው የፋይናንስ ቀውስ እንደ ትልቅ ምክንያትነት ሲጠቅሱ ይሰማል ::

ባለፉት ሶስት አመታት ላይ ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ፋሲል ከነማ ከአመት አመት የተሻለ ነጥቦችን ማስመዝገብ ከቻሉ ምርጥ ሶስት ቡድኖች ውስጥ ዋነኞቹ ናቸው ::

 

በምስሉ ላይ እንደተገለፀው ቅዱስ ጊዮርጊስ የተሻሉ ነጥቦችን ሲሰበስብ መቀለ 70 እንደርታ ሊጉን በተቀላቀለበት አመት ካስመዘገበው ጋር ተመሳሳይ ነጥብ ማሳካት ችሏል ::

ባለፉት ሶስት የውድድር አመታት ላይ በመጀመሪያ ዙር ውድድር ላይ ብዙ ነጥቦችን መሰብሰብ የቻሉ የመጀመሪያዎቹን ሶስት ክለቦች በምስል ልናደርስዎ ወድናል ::

ክለቦቹ ማግኘት ከሚገባቸው 135 ነጥቦች ከፍተኛ ሆኖ የተገኘው የመቐለ 70 እንደርታ ሲሆን 85 ነጥቦችን መሰብሰብ ችለዋል ::

በክፍል ሁለት ቁጥራዊ መረጃዎች ቀሪ የኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ ሁነቶች ይዘንላችሁ የምናቀርብ ይሆናል ::

Hatricksport website Editor

Twitter

kidus Yoftahe

Hatricksport website Editor