መነሻ ገጽ ሀትሪክ ስፖርትጋዜጣ የቅ.ጊዮርጊስ ደጋፊዎች ቡድናችንን ለመደገፍ ያደረግነው ጥረት የደ .አፍሪካ ኤምባሲ በፈጠረብን ችግር ምክንያት እንቅፋት እየፈጠረብን ነው በማለት ቅሬታቸውን አቀረቡ፤ኤምባሲው የቅ.ጊዮርጊስ ተጫዋቾች በአካል ካልመጡ ቪዛ አልሰጥም በማለቱ ተጫዋቾቹ ኤምባሲ ድረስ ለመሄድ ተገደዱ፤ቡድኑ ሐሙስ ረፋድ ላይ ይጓዛል
ሀትሪክ ስፖርትጋዜጣ

የቅ.ጊዮርጊስ ደጋፊዎች ቡድናችንን ለመደገፍ ያደረግነው ጥረት የደ .አፍሪካ ኤምባሲ በፈጠረብን ችግር ምክንያት እንቅፋት እየፈጠረብን ነው በማለት ቅሬታቸውን አቀረቡ፤ኤምባሲው የቅ.ጊዮርጊስ ተጫዋቾች በአካል ካልመጡ ቪዛ አልሰጥም በማለቱ ተጫዋቾቹ ኤምባሲ ድረስ ለመሄድ ተገደዱ፤ቡድኑ ሐሙስ ረፋድ ላይ ይጓዛል

አጋራ
አጋራ

በካፍ ቶታል ቻምፒየንስ ሊግ የምድብ ድልድል ውስጥ በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የገባው ኢትዬጵያዊው ቅ.ጊዮርጊስ ከማማሎዲ ሰንዳዉንስ ጋር ላለበት የምድቡ የመጀመሪያ ጨዋታ ከነ በስቲያ ሐሙስ ማለዳ ወደ ደ.አፍሪካ ይጋዛል።በርካታ ክለባቸውን ለማበረታታት ወደ.አፍሪካ ለመሄድ ዝግጅት ቢያደርጉም ኤምባሲው በፈጠረባቸው አላስፈላጊ መስፈርቶችና ጥያቄዎች መጉላላታቸውና እንቅፋት እየተፈጠረባቸው መሆኑን በተለይ ለሀትሪክ ድረ-ገፅ ገለፁ።
በሌላ በኩል የቅ.ጊዮርጊስ ተጫዋቾች በአካል ኤምባሲ ድረስ ካልመጡ ኤምባሲው ቪዛ አልሰጥም በማለቱ የቡድኑ ተጫዋቾች ኤምባሲው ድረስ ለመሄድ ተገደዋል።
ከክለቡ ደጋፌዎች ከተገኘው መረጃ ለማወቅ እንደተቻለው በርካታ ደጋፊዎች ወደ .አፍሪካ ተጉዘው ቡድናቸውን ለማበረታታት ፍላጎት ቢያሳዩም ኤምባሲው አሳማኝ ባልሆነ ምክንያት ጥያቄያቸውን ውድቅ በማድረጉ በርካታ ደጋፊዎች ከጉዞው መቅረታቸው ነው የተሰማው።

wp-image-233506766jpg.jpeg
ከዚሁ ከቅ.ጊዮርጊስ ዜና ጋር በተያያዘ ከማማሎዲ ሰንዳውንስ ጋር ላለባቸው ወሳኝ ጨዋታ ቡድኑ 18 ተጫዋቾችን ይዞ የሚጋዝ ሲሆን ሳላህዲን ሠይድ በሁለት ቢጫ፣በሐይሉ አሰፋ ቱሳ ምንተስኖት በጉዳትእ አብረው ከቡድኑ ጋር የማይጋዙ ሲሆን በጉዳት ምክንያት ለረዥም ጊዜ ከሜዳ ርቆ የነበረው ምን ያህል ተሾመ አብሮ ከቡድኑ ጋር የሚጓዝ መሆኑ ታውቋል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሀትሪክ ስፖርትጋዜጣዜና እረፍትዜናዎች

የጋዜጠኛ መሸሻ ወልዴ አጭር የህይወት ታሪክ

ጋዜጠኛ መሸሻ ወልዴ ከእናቱ ከወ/ሮ ጌጤ ገ/ስላሴ እና ከአባቱ ሀምሳ አለቃ ወልዴ...

ሀትሪክ ስፖርትጋዜጣ

ሀትሪክ አሁንም ቀጠሮ ማክበር ስልጣኔ ነው በሚለው አቋሟ ጸንታለች

ቅዳሜ ጠዋት በቀጠሮ  ቀናችን  እርስዎ ጋዜጣዋን በእጅዎ ያስገቡ እንጂ አዳዲስና ያልተሰሙ መረጃዎችን...

ሀትሪክ ስፖርትጋዜጣዜናዎች

ሀትሪክ አሁንም ቀጠሮ ማክበር ስልጣኔ ነው በሚለው አቋሟ ጸንታለች

ቅዳሜ ጠዋት በቀጠሮ  ቀናችን  እርስዎ ጋዜጣዋን በእጅዎ ያስገቡ እንጂ አዳዲስና ያልተሰሙ መረጃዎችን...