የቅዱስ ጊዮርጊስ እግር ኳስ ክለብ የሩጫ ውድድር አዘጋጅቷል።
በመጭው የካቲት አስራ ሁለት የሚጀምረው የቅዱስ ጊዮርጊስ እግር ኳስ ክለብ ቤተሰባዊ እሩጫ መነሻውን አራዳ አድርጎ ፍፃሜውን በሚሊኒየም አዳራሽ ያገኛል። በእለቱም የመዝናኛ ዝግጅቶች በሚሊኒዮም አዳራሽ ልዩ ልዩ ውድድሮች የህፃናት መዝናኛ እና አሳታፊ ፕሮግራሞች በማለፊያ አከባቢዎችን ጨምሮ ይከናወኑበታል። በሩጫው ሀያ ሺህ ሰዎች ይሳተፉበታል ተብሊ ሲጠበቅ። የውድድሩ አሸናፊዎችም ልዩ ሽልማት ሲበረከትላቸዋል። ውድድሩን የሚያጠናቅቁ ሁሉም ተሳታፊዎች የሜዳልያ ሽልማት እንደሚበረከትላቸው ሀትሪክ ስፖርት ያገኘችው መረጃ ያመላክታል። የትኬት ሽያጭ እና ዋጋው በቅርብ ቀን ይፋ ሲደረግ የመሮጫ ቲሸርቶች ግን ውድድሩ ሲቃረብ በተመረጡ ቦታዎች የሚሸጡ ይሆናል።
አስተያየት ይስጡ