አጋራ

በስምንተኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ከተመለከትናቸው ጨዋታዎች ትልልቅ ጉዳዮች ናቸው ያልናቸውን እንደሚከተለው አቅርበንላችኋል።

ድሎች

ከሀዋሳ ከተማና አዳማ ጨዋታ ውጭ ሁሉም ጨዋታዎች በመሸናነፍ ያለቁ ሲሆን ሶስት ክለቦች ደግሞ ከሜዳቸው ውጭ ጣፋጭ ሶስት ነጥብ ይዘው ወጥተዋል። ሲዳማ ቡናን በመርታት የአመቱን ድል ሀብሎ የጀመረው ሀድያ ሆሳእና ወደ ትግራይ አቅንቶ የሊጉን መሪ ወልዋሎ አዲግራት ዩንቨርሲቲን በፒስማርክ ኦፖንግ ብቸኛ ግብ ሁለተኛ ድሉን ማስመዝገብ ችሏል። ወላይታ ድቻ እና አዳማ ከተማ ደግሞ አሁንም ወደ ድል ለመመለስ እየተቸገሩ ይገኛሉ። በአንፃሩ መቐለ 70 እንደርታ ወልቂጤ ከተማን በማሸነፍ ሁለተኛ የሜዳ ውጭ ነጥቡን ማሳካት ሲችል። ሲዳማ ቡና ደግሞ ከተከታታይ የነጥብ ቀውስ ወደ ድል ተመልሰዋል።

ጎሎች

በዚህ ሳምንት በጠቅላላ 22 ግቦች ተቆጥረዋል። ከተቆጠሩት ግቦች መካከልም አምስቱ በፍፁም ቅጣት ምት የተቆጠሩ ሲሆን። ጌታነህ ከበደ በአራታኛው ደቂቃ ድሬዳዋ ላይ ያስቆጠረት ጎል ደግሞ የዚህ ሳምንት ፈጣኗ ግብ ሆና ተመዝግባለች። በዚህ ሳምንት ውድድር 20 ተጫዋቾች ግብ ሲያስቆጥሩ ጌታነህ ከበደ እና ሙጂብ ቃሲም ሁለት ሁለት ግቦች አስቆጥረው አራት ግቦች ሲመዘገቡ ቀሪዎቹ አስራ ስምንት ግቦች ግን በተለያዩ ተጫዋቾች የተመዘገቡ ናቸው። ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ ድሬዳዋ እና ሲዳማ ቡና ከ ባህርዳር በተደረገው ጨዋታ መካከል ደግሞ በርካታ ግቦች የተቆጠሩበት ጨዋታ ሆኖ ሲያልፍ ወልዋሎ ከ ሀድያ እና ወልቂጤ ከመቀለ 70 እንደርታ መካከል የተደረገው ጨዋታም ዝቅተኛ ግብ የተስተናገደበት ሆኖ አልፏል።

ግብ ጠባቂዎች

የአብዱልአዚዝ ኬይታን ቅጣት ተከትሎ ወደ ቋሚ ተሰላፊነት የመጣው የወልዋሎ አዲግራት ዩንቨርሲቲው ግብ ጠባቂ ጃፋር ደሊል ለሁለት ጨዋታዎች ግቡን ሳያስደፍር ቢወጣም ለበፒስማርክ ኦፖንግ ግን እጁን ሰጥቷል። ጥሩ መነቃቃት ላይ የነበረው የሀዋሳው ግብ ጠባቂ ኢኖህ ቤሊንጋ ዛሬም ጥሩ አቋሙን ያሳያል ተብሎ ቢጠበቅም በመጀመሪያው ግማሽ ባጋጠመው ጉዳት ተቀይሮ ወጥቷል።

የቀድሞ የፈረሰኞቹ አሰልጣኝ ሚሉቲን ሚቾ በአዲስ አበባ መገኘት

የቀድሞው የቅዱስ ጊዮርጊስና የኡጋንዳ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ በቅርቡ ከግብጹ ዛማሌክ ከኃላፊነታቸው መነሳታቸውን ተከትሎ ብሎም የፈረሰኞቹን ጨዋታ ለመመልከት አዲስ አበባ ስታዴም መገኘታቸውን ቅዱስ ጊዮርጊስን ሊረከቡ ይችላሉ የሚሉ ግምቶች እየመጡ ይገኛሉ። ዛሬ በአዲስ አበባ ስታዲየም ተገኝተው የክለቡን ጨዋታ የተመለከቱት ሚቾ ክለቡን ከተረከቡ የውጤት ቀውስ ውስጥ ያለውን ክለብ ሊታደጉት ይችላሉ።

ከክለቡ ጋር በርካታ ድሎችን ማጣጣም የቻሉት ሚቾ ለክለቡ ከፍተኛ ፍቅር እንዳላቸው በበርካታ አጋጣሚዎች ሲናገሩ ተደምጠዋል። ዛሬ በአዲስ አበባ ስታዲየም በተገኙበትም ወቅት በደጋፊው የተደረገላቸው ከፍተኛ እቀባበል ቡድኑን ሊረከቡ እንደሚችሉ አዝማሚያዎች ያሳያሉ።

ተጫዋቾች

ሙጂብ ቃሲም እና አማኑኤል ገ/ሚካኤል አሁንም ግብ ማምረታቸውን ቀጥለውበታል በዚህ መንገድ የሚቀጥ ከሆነ የኮከብ ግብ አግቢነቱ ከሁለቱ እንደማልፍ ምንም የሚያጠያይቅ ጉዳይ አይደለም።

የአሰልጣኞች አስተያየት

አሁንም የጅማ አባጅፋሩ አሰልጣኝ ጳውሎ ጌታቸው (ማንጎ) ከጨዋታ ጨዋታ እየሰጣቸው ያሉ አስተያየቶች አሁንም በአስገራሚነታቸው እየቀጠሉ ነው። ትላንት በሰበታ ከተማ 3-1 ከተሸነፉ በኋላ ከአስራ ስድስቱ የሊጉ ክለቦች 74 ስአታት ሳናርፍ ተከታታይ ጨዋታዎች ያደረግነው እኛ ብቻ ነን ብለዋል። በአንፃሩ ተጋጣሚያችን ደግሞ 96 ስአታትን አርፈው ነው ለጨዋታ የቀረቡት። በህጉ መሰረት ደግሞ 72 ስአታት ማረፍ ነበረብን በህጉ ከሄድን ይህን ጨዋታ ማድረግ አልነበረብንም ብለዋል።

መርሀግብሩን ለምን አላስቀየራችውም ተብለው ሲጠየቁም?

በስራአስኪያጃችን በኩል አስጠይቀን የነበርን ቢሆንም። ሜዳው ነገ ይያዛል ስለተባልን ምንም ማድረግ ስለማንችል ተጫውተናል። ይህ ስለተሸነፍን ለምክንያትነት ያቀረብኩት አይደለም በቀጣይ ወደ አሸናፊነት ለመመለስ የተቻለንን እናደርጋለን ሲሉም አክለዋል።

የአሰልጣኞች ስንብት

በነጥብ እጦት ውስጥ የሚገኙት የወላይታ ድቻው አሰልጣኝ ገብረክርስቶስ ቢራራ የመጨረሻ የሊግ ጨዋታቸው ሊሆን ይችላል ተብሎ ይገመታል። እንዳማሳያነትም ድች በደረጃ ሰንጠረዡ በ8 ነጥብ ግርጌ ላይ ይገኛል። በስተመጨረሻም ትላንት ከጨዋታው መጠናቀቅ በኋላ ከክለቡ ጋር እንደማይቀጥሉም አሳውቀዋል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየዲሲፕሊን ውሳኔዎችዲሲፕሊን ውሳኔ

የ32ኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

የዲሲፕሊን ውሳኔዎች አህመድ ረሺድ (ድሬደዋ ከተማ) : በኢትዮጵያ ዋንጫ ውድድር 1 እንዲሁም...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሀምራዊ ለባሾቹ እና የጣና ሞገዶቹ ጣፋጭ ሦስት ነጥብን ወደ ቋታቸው ከተዋል

በሊጉ የሳምንቱ የሁለተኛ ቀን ጨዋታ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ባህርዳር ከተማ ወሳኝ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሲዳማ ቡና ሲሸነፍ በተጠባቂው ጨዋታ መቻል በጎል ፌሽታ ነገሌን ረቷል

በሳምንቱ የመጀመሪያ ቀን ጨዋታ የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና በሀድያ ሆሳዕና ሽንፈት ሲያስተናግድ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

ውጤት ለውጧል የተባለው ዳኛ ተባረረ

በዮሴፍ ከፈለኝ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውጤት ለውጠዋል የተባሉ አርቢትሮችን ወደመጡበት መመለሱን አሁንም ቀጥሏል። ከቀናት...