የማክሰኞ ሀትሪክ ጋዜጣዎ በነገው እትሟ
ሀትሪክ ስፖርት ዘወትር ማክሰኞ ለንባብ የምትበቃ ተወዳጅ እና ባለቀለም ጋዜጣ ስትሆን በነገው እትሟም ለእናንተ ውድ አንባቢዎቿ የምትወዱትን የተለያዩ የሀገር ውስጥ እና የባህር ማዶ ዘገባዎችን ልታስነብቦት መሰናዶዋን አጠናቃለች፡፡
ሀትሪክ በሀገር ውስጥ የነገው እትሟ ምን ምን ጉዳዮችን ይዛ ይሆን?
ከፍተኛ ተወዳጅነትን ባተረፈላት THE BIG INTERVIEW ዓምዷ የኢትዮጵያ ቡናና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ተጨዋች ከሆነው አህመድ ረሺድ /ሺሪላ/ ጋር የተለያዩ ሀሳቦችን በማንሳት ሰፊ ቆይታን ያደረገች ሲሆን በፕሪምየር ሊጉ የዘንድሮ የውድድር ዘመን የክላባቸው ተሳትፎ እና በራሱ የኳስ ሕይወት ዙሪያም ከመቐለ 70 እንደርታው ጠንካራ የተከላካይ ስፍራው ተጨዋች አሚን ነስሩም ጋር ሀትሪክ ቆይታ አላት፤ ተጨዋቾቹ ምን ብለው ይሆን?
ሀትሪክ በባህር ማዶ ዘገባዎቿም ነገና ረቡዕ በሚካሄዱት ወሳኝ የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታዎችና በሳምንቱ የመጨረሻ ቀናቶችም ስለተካሄዱት የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ እና የሌሎች የአውሮፓ ሊግ ጨዋታዎች ዙሪያም ሲያነቡት ሊወዱት የሚችሉትን ዘገባ ይዛሎት ቀርባለች፡፡
ሀትሪክ የእናንተው ናት አታምልጦት፡፡
ሀትሪክን ከሳምንታዊ ጋዜጣዋ በተጨማሪ http://www.hatricksport.com/ ድረ-ገፃችን ላይ አዳዲስና ወቅታዊ መረጃዎችን ያገኛሉና አሁኑኑ ድረ-ገፃችንን ይጎብኙ፤ የሀትሪክ ቤተሰብም ይሁኑ፡፡
የሀትሪክ ጋዜጣ የነገው የፊት ለፊት ገፅ ይህንን ይመስላል፡፡
አስተያየት ይስጡ