ለ25ኛ ጊዜ በጣሊያኗ ሮም ከተማ ትናንት በተካሄደ የማራቶን የሩጫ ውድድር በሁለቱም ጾታ ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች አሸናፊ ሆነዋል።
በውድድሩ በወንዶች ኢትዮጵያዊው አትሌቶች ከአንደኛ እስከ አምስተኛ፤ በሴቶች ደግሞ ከአንደኛ እስከ ሶስተኛ ያለውን ደረጃ ይዘው አጠናቀዋል።
በወንዶች መካከል በተደረገው የማራቶን ውድድር አትሌት ፀበሉ ዘውዴ 2 ሰዓት ከ8 ደቂቃ ከ37 ሰከንድ በሆነ ሰዓት አሸናፊ ሆኗል።
እንዲሁም አትሌት ተስፋ ጥሩነህ 2 ሰዓት ከ9 ደቂቃ ከ17 ሴኮንድ በመግባት በሁለተኛ፣ አትሌት ይሁንልኝ አዳነ ደግሞ 2 ሰዓት ከ9 ደቂቃ ከ 53 ሴኮንድ ሶስተኝነትን የዞ ውድድሩን አጠናቋል።
- ማሰታውቂያ -
አትሌት ሙሳ ባቦና አትሌት ብርህኑ ተሾመ ከኢትዮጵያ እንደ የቅድም ተከተላቸው አራተኛና አምስተኛ ወጥተዋል።
በሴቶች መካከል የተደረገውን የማራቶን ውድድር ደግሞ አትሌት መገርቱ አለሙ 2 ሰዓት ከ22 ሴኮንድ ከ 52 ደቂቃ አንደኛ በመሆን አሸንፋለች።
አትሌት ሙሉሀብት ፀጋ 2 ሰዓት ከ26 ደቂቃ ከ41 ሴኮንድ በሁለተኝነት እንዲሁም አትሌት ጫልቱ ነገሰ 2 ሰዓት ከ30 ደቂቃ ከ45 ሴኮንድ በሆነ ሰዓት ሶስተኛ ደረጃን በመያዝ ውድድሩን በበላይነት አጠናቀዋል።