መነሻ ገጽ The BiG Interview የመጀመሪያዋ ባለቀለምና ተወዳጇ ሀትሪክ ሳምንታዊ የስፖርት ጋዜጣ እንደተለመደው አዳዲስና ትኩስ ዘገባዎችን አካታ ነገ ማለዳ እጅዎ ትገባለች ይጠብቃት ።
The BiG Interviewሀትሪክ ስፖርትጋዜጣኢትዮጵያን በውጪዜናዎች

የመጀመሪያዋ ባለቀለምና ተወዳጇ ሀትሪክ ሳምንታዊ የስፖርት ጋዜጣ እንደተለመደው አዳዲስና ትኩስ ዘገባዎችን አካታ ነገ ማለዳ እጅዎ ትገባለች ይጠብቃት ።

አጋራ
አጋራ

የመጀመሪያዋ ባለቀለምና ተወዳጇ ሀትሪክ ሳምንታዊ የስፖርት ጋዜጣ እንደተለመደው አዳዲስና ትኩስ ዘገባዎችን አካታ ነገ ማለዳ እጅዎ ትገባለች ይጠብቃት ።
ሎዛ አበራ በቀጥታ በስልክ በተለይ ለሀትሪክ
ሀትሪክ ስፖርት በነገው እትማ አዲስ ነገር ይዛ ብቅ ትላለች በተወዳጂና በርካታ ተከታታዮች ባሉት The Big Interview አምዳ ወደ ማልታ በቀጥታ ስልክ በመደወል በማልታ ሰማይ ስር እያንፀባረቀች አዳዲስ ታሪኮችን እያፃፈች ያለችውን ሎዛ አበራን አነጋግራ በርካታ ቁም ነገሮችን ልታስነብበን መስናዶዋን አጠናቃለች።
የሀትሪክ ጋዜጣ ኤክስኪዩቲቭ ኤዲተር የሆነው ጋዜጠኛ ይስሀቅ በላይ በማልታ ሊግ የጎል ዝናብ እያወረደች ያለችውን የግብ ማሽን በማልታ አዲሱ የፕሮፌሽናል ህይወታ ዙሪያ ጣፋጭ ቆይታ አድርጋል ሎዛ ምን ብላው ይሆን?የነገዋ ሀትሪክ በፍፁም እንዳታመልጥዎ።በሌላ የሀገር ውስጥ ዜና የአዲስ ፍልስፍና ባለቤት የሆነውና ከ3 ጨዋታ በሃላ ወደአሽናፊነት የተመለሰው ኢትዮጵያ ቡናና በሜዳው ከሽሬ ጋር ነጥብ በመጋራቱ ከደጋፊው የጠነከረ ተቃውሞ በቀረበባቸው ቅ.ጊዮርጊሶች ዙርያ ዘገባዎችን አካታለች።የኢት.ቡናው አቤልና የቅ.ጊዮርጊሱ ምንተስኖት አዳነ በውጤቶቻቸው ዙርያ ለሀትሪክ ተንፍሰዋል ለመሆኑ ምን ብለው ይሆን?ነገ ማለዳ ሀትሪክ መልሱን ይዛ ብቅ ትላለች እንዳታመልጥዎ።
ሀትሪክ በባህር ማዶ ዘገባዋስ ምን ታስነብቦት ይሆን? የአለም የክለቦች ሻምፒዮን በመሆን አዲስ ታሪክ ያፃፈው ሊቨርፑልና በፊርሚኖ ዙርያ እንዲሁም በአዲሱ የሊቨርፑል ፈራሚ በታኩሚ ሚናሚኖ ዙርያ አዲስና ያልተሰማ ልዩ ቃለ-ምልልስ የሊዮኔል ሜሲ አዲስና ጣፋጭ ቃለ-ምልልስ እንዲሁም የአርሴናል አዲሱ አለቃ በአርቴታ ዙርያ አዳዲስ ዘገባዎችን የያዘች ሲሆን የቼልሲ ድልም እንዲሁ ተመሳሳይ ሽፋን ተሰጥቶታልና
የነገዋ ሀትሪክ ሌላም የሚወዱትን ዘገባ ይዛሎት ቀርባለችና በፍፁም እንዳታመልጥዎ። ሀትሪክ አ
የሀትሪክ ስፖርት የነገው የፊት ለፊት ገፅ ይህንን ይመስላል።
ሀትሪክን ከጋዜጣዋ በተጨማሪ ከፍተኛ መሻሻል ባሳየውና በአጭር ጊዜ በርካታ ጎብኚዎች ባሉት በድረ-ገፅዋ hatricksport.net አዳዲስ መረጃዎችን ያገኛሉና ዛሬውኑ ይጎብኙን።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየዲሲፕሊን ውሳኔዎችዲሲፕሊን ውሳኔ

የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

ገዛኸኝ ደሳለኝ (ሸገር ከተማ) : ክለቡ ከ ኢትዮጵያ ቡና ጋር ባደረገው የ26ኛ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና በዝናባማው ጨዋታ በመቻል ሲረታ የጣናው ሞገድም አሸንፏል

እጅግ በከባድ ዝናብ ታጅቦ በተደረገው ጨዋታ መቻል የሊጉን መሪ ሲዳማ ቡናን 3ለ1...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሀድያ ሆሳዕና ፣ ፋሲል ከነማ እና ወላይታ ድቻ ወሳኝ ድል አግኝተዋል

በሊጉ የሳምንቱ የሁለተኛ ቀን መርሀግብር ሀዋሳ ከተማ ወደ ሊጉ መሪ የሚጠጋበትን ዕድል...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ፈረሰኞቹ በድል ሲቀጥሉ ንግድ ባንክ እና ድሬዳዋም አሸንፈዋል

ቅዱስ ጊዮርጊስ ተከታታይ ድሉን ወደ ቋቱ ሲከት ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከጨዋታ ብልጫ...