የሐዋሳ ከተማው ኮከብ የውጭ ዕድልን አግኝቷል !

ያለፊትን ዓመታት በኢትዮጵያ ፕርሚየር አንፀባራቂ ብቃቱን ማሳየት የቻለው የፊት መስመር አጥቂው መስፈን ታፈሰ ከኢኳቶሪያል ጊኒው ፉትሮ ኪንግስ የሙከራ ዕድል ማግኘቱን የተጫዋቹ ወኪል አቶ ሳምሶን ነስሮ ነግረውናል ።

መስፈን ታፈሰ በዛሬው ዕለት ወደ ማላቡ ያቀና ሲሆን አምስት ቀናቶችን ልምምድ ከሰራ በኋላ ወደ ካሜሮን ድዋላ በማቅናት ክለቡ ከካሜሩን የሊጉ ሻምፒዮን ጋር በሚኖረው የወዳጅነት ጨዋታ ላይ እንደሚሳተፍ የሰርነስ ሶከር ኤጀንሲ ባለቤት እና የተጫዋቹ ወኪል አቶ ሳምሶን ነስሮ አሳውቀውናል ።

መስፈን ታፈሰ ከፉትሮ ኪንግስ በተጨማሪም ከ ግሪክ እና ጣልያን ክለቦች በመስፍን ታፈሰ ላይ ፍላጎት ያሳዩ የአውሮፓ ሀገራት መካከል ዋነኞቹ ሲሆኑ ወደ እዛ የማምራት እድልም ሊኖረው እንደሚችል ታውቋል ።

Hatricksport website Editor

Twitter

kidus Yoftahe

Hatricksport website Editor