የሊግ ካምፓኒው የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ የማስተላለፍ መብትና የፕሪሚየር ሊጉ ስያሜ ባለቤትነትን አስመልክቶ ያወጣውን ጨረታ አስተላለፈ

 

ከሣምንት በፊት የሊግ ካምፓኒው 16ቱ የፕሪሚየር ሊግ ክለቦች በሜዳና ከሜዳ ውጭ የሚያደርጉትን የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ የማስተላለፍ መብት (Broadcast) እና የፕሪሚየር ሊጉ ስያሜ ባለቤትነትን (Title Sponsor) የመሆን ፍላጎት ያላቸው ኩባንያዎች እንዲሳተፉ የሚጋብዝ የጨረታ ማስታወቂያ ማውጣቱንና ጨረታውም እ,ኤ,አ ማርች 30 እንደሚከፈት ገልፀን ዘግበን ነበር።

የፕርምዬር ሊግ ካምፓነ ያወጣው ይሄንን ጨረታ ተከትሎ ጨዋታ የማስተላለፍ ከፍተኛ ልምድና የገንዘብ አቅም ያላቸው በርካታ ታላላቅ ኩባንያዎች ፍላጎት ማሳየተቸውን ጠቅሰን ግን አለም በኮሮና ቫይረስ ጭንቀት ውስጥ ወድቃ፣ የዓለም ብቻ ሣይሆን የሀገራችን ሊግም ተቋርጦ ብቻ ሳይሆን መቼ እንደሚጀመር በግልፅ ባልታወቀበት እንዲሁም የኢትዮጵያ አየር መንገድን ጨምሮ በርካታ አየር መንገዶች በከፊልና መሉ በሙሉ በረራቸውን እየሰረዙ ባለበት ወቅት ጨረታውን በተጠቀሰው ቀን ማርች 30 ማካሄድ ነገሮችን አስቸጋሪ እንደሚያደርግና የጨረታው መክፈቻ ቀን ቢተላለፍ መልካም ነው በሚል መዘገባችንም የሚዘነጋ አይደለም።

ይህ ዘገባ ለንባብ ከበቃ በሃላ ባገኘነው ዜና መሠረት የሊግ ካምፓኒ ወቅታዊውን የአለማችንን ችግር ግምት ውስጥ በመክተትና መተላለፍ አለበት የሚል ድምዳሜ ላይ በመድረሳቸው የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታን የማስተላለፍ መብት (Broadcast)፣የፕሪሚየር ሊጉ የስያሜ መብት(Title Sponser)ን አስመልክቶ ያወጣውንና ማርች 30 ይከፈታል በሚል ያወጣውን ጨረታ ላልተወሰነ ጊዜ ማራዘሙ ታውቋል።የሊግ ካምፓኒው በጨረታው ለመሳተፍ ፍላጎት ላሳዩት ኩባንያዎችና ተወካዮቻቸው ጨረታው በተጠቀሰው ቀን እንደማይከፈት ከመግለፁ ውጪ ጨረታው መቼ እንደሚከፈት የገለፀው ነገር ግን የለም።


የጨረታ ማስታወቂያ ማውጣቱንና ጨረታውም እ,ኤ,አ ማርች 30 እንደሚከፈት  የዘግበንበትን ዜና ለማግኘት ምስል ያለውን ሊንክ ይጫኑ 👇

 

https://www.hatricksport.net/የሊግ-ካምፓኒ-ኃላፊዎችና-የፌዴሬሽኑ-ፕሬ/

Hat-trick Weekly Sport Newspaper Founder & Managing Editor.
The First Color Sport Newspaper in the country.

Yishak belay

Hat-trick Weekly Sport Newspaper Founder & Managing Editor. The First Color Sport Newspaper in the country.