መነሻ ገጽ ለገጣፎ ከተማ የ2010 የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግን አሸንፈን ፕሪሜየር ሊግ አንገባለን! የለገጣፎ ከተማ አስልጣኝ ያሬድ ቶሌራ
ለገጣፎ ከተማየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

የ2010 የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግን አሸንፈን ፕሪሜየር ሊግ አንገባለን! የለገጣፎ ከተማ አስልጣኝ ያሬድ ቶሌራ

አጋራ
አጋራ

​ለገጣፎ ከተማ በ2008 ከ ከአንደኛው ሊግ ወደ ከፍተኛ ሊጉ እንዲቀላቀል እንዲሁም በ2009 የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ በ30ጨዋታዎች በ10 የጎል ክፍያ በ46 ነጥብ የምድብ ሀ ደረጃ ሰንጠረዡን በአራተኛ እንዲያጠናቅቅ ትልቁን ድርሻ  የሚወሰደው የቡድኑ ዋና አሰልጣኝ ያሬድ ቶሌራ ነው፡፡ ቅድመ የውድድር ዘመን ዝግጅቱን እና ቀጣይ እቅዱን በተመለከተ ከሀትሪክ ስፖርት ድህረ-ገፅ ጋር አጭር ቆይታ አድርጓል፡፡  

የቅድመ የውድድር ዝግጅታችሁ ምን ይመስላል?

:-ከባለፈው አመት በተለየ ዘንድሮ 14 አዳዲስ ልጆችን እና 11 ነባር ተጫዋቾችን መያዝ ችለናል፡፡ ከዝግጅት መልስም 3 የወዳጅነት ጨዋታዎችን ማድረግ ችለናል በአሁኑ ሰዓት ደግሞ ለ6ኛ ግዜ የኦሮሚያ ሲቲ ካፕ ላይ በመሳተፍ ላይ እንገኛለን፡፡

የከተማው አስተዳደር  ድጋፍ ምን ይመስላል?
:- ድጋፍን በተመለከተ የከተማው አስተዳደር ከባለፈው ዓመት የተሻለ ባጀት መድበውልናል፡፡ ይህም ከኛ የተሻለ ውጤት ይጠብቃሉ ፡፡የደጋፊ ማሀበርም ተቋቁሟል ውድድር ሲጀመር እምናየው ይሆናል፡፡

በለገጣፎ ቡድን ውስጥ ትልቁ የተጫዋቹ ክፍያ እንዲሁም ትንሹ ስንት ነው?
:- ተጫዋቾቹ ደሞዝ ከባለፈው አመት በታሻለ  መክፈል ጀምረናል፡ ቡድናችን ውስጥ ትልቁ  25,000 ብር ሲሆን ዝቅተኛው ደግሞ፡10,000 ብር ክፍያ ነው እምንከፍለው፡፡

በ2010 የውድድር ዘመን ያስቀመጣችሁት እቅድ እስከ ምን ድረስ ነው?
ከ2008 የወድድር ዘመን ወደ 2009 ስንመጣ ጥሩ ተፎካካሪ ሆኖ ማጠናቀቅ ነበር ያንን ማሳካት ችለናል፡፡ለ2010 የኢትዮጵያ ከፍተኛው ሊግ የውድድር ዘመን ጥሩ ተፎካካሪ ሆነን ፈጣሪ ከረዳን ፕሪሜየር ሊግ ለመግባት እንሞክራለን፡፡

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

አሰልጣኝ ጳውሎስ (ማንጎ) ከአምስት ጨዋታዎች በኋላ ተሰናበቱ

አዲስ የተቀጠሩት እና ዛሬ ቡድኑን የመሩት አሰልጣኝ መሳይ በየነ ቡድኑን በአንድ ጨዋታ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

ለሌብነት ምቹ ወደ መሆን የቀረበው የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ?

ለወትሮ ሀሜት የማያጣው የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ትኩረት ሊሰጠው ወደ ሚገባው ምዕራፍ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

ሦስት ስመ ጥር አሰልጣኞች ሦስት ክለቦች ለማትረፍ በሀላፊነት ተረክበዋል

ላለመውረድ እየተጫወቱ የሚገኙ ሦስት የከፍተኛ ሊግ ክለቦች በሦስት የሚታወቁ አሰልጣኞች ይመራሉ። በኢትዮጵያ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግጋሞ ጨንቻ

የጋሞ ጨንቻው ወጣቱ አሰልጣኝ ማነው ?

ራሱ የመሠረተውን ክለብ ወደ ፕሪምየር ሊጉ እያንደረደው የሚገኘው አሰልጣኝ። ከአመት አመት አዳዲስ...