መነሻ ገጽ ዜናዎች ዝውውር / ፋሲል ከተማ ዩጋንዳዊውን አጥቂ ሀሚዝ ኪዛ አስፈረመ
ዜናዎችየዝውውር ዜናዎች

ዝውውር / ፋሲል ከተማ ዩጋንዳዊውን አጥቂ ሀሚዝ ኪዛ አስፈረመ

አጋራ
አጋራ

ፋሲል ከተማ ዩጋንዳዊውን አጥቂ ሀሚዝ ኪዛ በ2 ዓመት ኮንትራት ውል አስፈርሟል፡፡

አፄዎቹ በአሁኑ የዝውውር መስኮት የተጨዋቾችን ውል በማቋረጥ እና አዳዲስ ተጨዋቾችን በማስፈረም ስራ ላይ ተጠምደዋል፡፡

ፋሲል ከተማ  ባለፈው ሳምንት ኬኒያዊውን የመሃል ተከላካይ ተጨዋች ሰንደይ ሙቱኩን ከድሬድዋ  ከተማ ሲያስፈርሙ በሌላ በኩል በክረምቱ የዝውውር መስኮት ያስፈረሟቸውን 3 ተጨዋቾች የዳዊት እስጢፋኖስ ፡አቤል ውዱና የናይጄሪያዊውን ሮበርት ሴንቴንጎ ውል በስምምነት  በማቋረጥ መለያየታቸው ይታወሳል፡፡ 
ፋሲል ከተማ በሁለተኛው ዙር ተጠናክሮ ለመቅረብ በተለይም የአጥቂ ክፍሉን ለማጠናከር በአፍሪካ ሻምፒዬንስ ሊግና በኮንፌዴሬሽን ካኘ በመጫወት በርካታ ልምድ ያካበተውን ዩጋንዳዊ የፊት መስመር ተሰላፊ ሀሚዝ ኪዛን በ2 ዓመት ኮንትራት ውል አስፈርሟል፡፡
ሀሚዝ ኪዛ ለሀገሩ ዩጋንዳ ብሄራዊ ቡድን እና ለሀገሩ ዩአርኤ እግር ኳስ ክለብ የተጫዎተ ሲሆን ከሀገሩ ውጭ ለደቡብ አፍሪካው ፍሪ ስቴት ስታር ለሱዳኑ አልሂላል አልኦቢድ በተጨማሪም ለታንዛኒያዎቹ ያንግ አፍሪካ እና ሲምባ ክለቦች የተጫዎተ ድንቅ የአጥቂ ስፍራ ተጨዋች ነው፡፡

 

ሀሚዝ ኪዛ አፄዎቹን በ2 ዓመት ኮንትራት ውል ሲቀላቀል የአጥቂ ክፍሉን እንደሚያጠናክር ተስፋ ተጥሎበታል፡፡

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሀድያ ሆሳዕና ፣ ፋሲል ከነማ እና ወላይታ ድቻ ወሳኝ ድል አግኝተዋል

በሊጉ የሳምንቱ የሁለተኛ ቀን መርሀግብር ሀዋሳ ከተማ ወደ ሊጉ መሪ የሚጠጋበትን ዕድል...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ፈረሰኞቹ በድል ሲቀጥሉ ንግድ ባንክ እና ድሬዳዋም አሸንፈዋል

ቅዱስ ጊዮርጊስ ተከታታይ ድሉን ወደ ቋቱ ሲከት ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከጨዋታ ብልጫ...

ዋልያዎቹዜናዎችየኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን

አንጋፋው አሰልጣኝ በስማቸው የእግር ኳስ ማሰልጠኛ አካዳሚ ሊገነባላቸው ነው

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የቀድሞ አሰልጣኝ ኢንስትራክተር ሰውነት ቢሻውን ለማመስገን እና ዕውቅና ለመስጠት...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየዲሲፕሊን ውሳኔዎችዲሲፕሊን ውሳኔ

የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

1. ፉአድ ኢብራሂም (ኢትዮጵያ ቡና) : ከታች በተጠቀሱት 5 ጨዋታዎች የቢጫ ማስጠንቅቂያ...