ወልድያ ስፖርት ክለብ በ 3 ተጨዋቾቹ ላይ በየትኛውም እግር ኳስ ክለብ ለ2 ዓመት እንዳይጫዎቱና የገንዘብ ቅጣት ውሳኔ አሳልፏል፡፡
ወልድያ ስፖርት ክለብ ከወራቶች በፊት በወልዲያ ከተማ በነበረው ወቅታዊ ሁኔታ የክለቡ አጠቃላይ አባላት ወደየ ቤተሰቦቻቸው ተመልሰው ክለቡ መበተኑ የሚታወስ ሲሆን በከተማው የነበረው ወቅታዊ ሁኔታ ወደነበረበት ሲመለስ ክለቡ ከተጨዋቾቹ ጋር በመነጋገር ጥሪ በማድረግ ተጨዋቾች ወደ ካፕ በመመለስ መደበኛ ልምምድና የሊግ ጨዋታዎችን በተስተካካይ መርሃ ግብር እየተጫዎተ መሆኑ የሚታወቅ ነው፡፡
የወልዲያ ስፖርት ክለብ ቦርድ 3ቱ ተጨዋቾች ወደ ክለባቸው ባለመመለሳቸው ክለቡ እያደረጋቸው ባለው ቀሪ ተስተካካይ ጨዋታዎች ቡድኑ የተጨዋች አማራጭ እንዳይኖረው ከማድረጋቸው ባለፈም የክለቡን ጥሪ ባለማክበር ወደ ካፕ ባልተመለሱት
በተጨዋች ታደለ ምህረቴ፡ፍፁም ገ/ማርያምና፡ያሬድ ብርሃኑ ላይ የክለቡ ቦርድ ዛሬ ባሳለፈው የቅጣት ውሳኔ እያንዳንዳቸው ብር 150,000,00(አንድ መቶ ሃምሳ ሺ) እንዲቀጡና ለ2 ዓመት በየትኛውም እግር ኳስ ክለብ እንዳይጫዎቱ የእገዳ ውሳኔ አሳልፏል፡፡