መነሻ ገጽ ሀዋሳ ከተማ ዜና | በ12ኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የተሰረዙት 4ጨዋታዎች የሚካሄዱበት ቀን እና ሰዓት ታወቀ።
ሀዋሳ ከተማመቐለ ከተማመከላከያቅዱስ ጊዮርጊስኢትዮ-ኤሌክትሪክኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግደደቢትድሬዳዋ ከተማ

ዜና | በ12ኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የተሰረዙት 4ጨዋታዎች የሚካሄዱበት ቀን እና ሰዓት ታወቀ።

አጋራ
አጋራ

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 12ኛው ሳምንት ባሳለፍነው ቅዳሜ እና ዕሁድ(ጥር 12 እና 13 2010ዓ.ም) አ/አ ላይ ሊደረጉ የታሰቡት አራት ጨዋታዎች (ኢትዮጵያ ቡና ከ ሀዋሳ ከተማ፣ ኢትዮ- ኤሌክትሪክ ከ ድሬዳዋ ከተማ፣ መከላከያ ከ መቐለ ከተማ እና ቅ/ጊዮርጊስ ከ ደደቢት) በቂ የፀጥታ ሀይል ባለመኖሩ ምክንያት ላልተወሰነ ጊዜ መራዘማቸውን መዘገባችን ይታወሳል።

ሆኖም ከኢትዮጵያ እግርኳስ ፌደሬሽን የውድድር እና ስነ ስርዓት ኮሚቴ ዛሬ በደረሰን መረጃ መሰረት እነዚህ ጨዋታዎች የሚደረጉበት ቀን እና ሰዓት ታውቋል። ስለዚህም እነዚህ ተሰርዘው የነበሩ ጨዋታዎች የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 1ኛ ዙር ከተጠናቀቀ በኋላ እንደሚከናወኑ የደረሰን መረጃ ያሳያል። በዚህም መሰረት መከላከያ ከ መቐለ ከተማ እሁድ የካቲት 11/2010ዓ.ም በ11:00 ኢትዮ- ኤሌክትሪክ ከ ድሬዳዋ ከተማ ሰኞ የካቲት 12/2010ዓ.ም በ11:00 ኢትዮጵያ ቡና ከ ሀዋሳ ከተማ ሀሙስ የካቲት 08/2010ዓ.ም በ8:00 እንዲሁም በጉጉት ተጠብቆ የነበረው የቅ/ጊዮርጊስ እና የደደቢት ጨዋታ ደግሞ እሁድ የካቲት 18/2010ዓ.ም በ11:00 ሰዓት የሚደረጉ እንደሚሆን ከኢትዮጵያ እግርኳስ ፌደሬሽን የውድድር እና ስነ ስርዓት ኮሚቴ የወጣው ፕሮግራም ያሳያል። ከላይ የተጠቀሱት አራቱም ጨዋታዎች በአ/አ ስታዲየም የሚከናወኑ ይሆናል።

በሌላ ዜና ድሬ ላይ ሰኞ(ጥር 21/2010ዓ.ም) ሊደረግ ቀጠሮ ተይዞለት የነበረው የድሬዳዋ ከተማ እና ኢትዮጵያ ቡና ጨዋታ ወደ ቅዳሜ(ጥር 19/2010ዓ.ም) እንዲሁም እሁድ (ጥር 20/2010ዓ.ም) ሊደረግ የነበረው የደደቢት እና የጅማ አባጅፋር የአ/አ ስታዲየም ጨዋታ ወደ ረቡዕ (ጥር 23/2010ዓ.ም) የተቀየሩ ጨዋታዎች ሲሆኑ በማግስቱ ሀሙስ(ጥር 24/2010ዓ.ም) ደግሞ ቅ/ጊዮርጊስ ከ ድሬዳዋ ከተማ የሚያደርጉት የአንደኛ ሳምንት ተስተካካይ ጨዋታ የሚከናወን ይሆናል።

ከ13ኛ ሳምንት ጀምሮ ያሉ ሙሉ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ከዚህ እንደሚከተለው ይሆናሉ።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሀድያ ሆሳዕና ፣ ፋሲል ከነማ እና ወላይታ ድቻ ወሳኝ ድል አግኝተዋል

በሊጉ የሳምንቱ የሁለተኛ ቀን መርሀግብር ሀዋሳ ከተማ ወደ ሊጉ መሪ የሚጠጋበትን ዕድል...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ፈረሰኞቹ በድል ሲቀጥሉ ንግድ ባንክ እና ድሬዳዋም አሸንፈዋል

ቅዱስ ጊዮርጊስ ተከታታይ ድሉን ወደ ቋቱ ሲከት ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከጨዋታ ብልጫ...

ዋልያዎቹዜናዎችየኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን

አንጋፋው አሰልጣኝ በስማቸው የእግር ኳስ ማሰልጠኛ አካዳሚ ሊገነባላቸው ነው

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የቀድሞ አሰልጣኝ ኢንስትራክተር ሰውነት ቢሻውን ለማመስገን እና ዕውቅና ለመስጠት...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየዲሲፕሊን ውሳኔዎችዲሲፕሊን ውሳኔ

የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

1. ፉአድ ኢብራሂም (ኢትዮጵያ ቡና) : ከታች በተጠቀሱት 5 ጨዋታዎች የቢጫ ማስጠንቅቂያ...