በ22ኛው የቶታል የአፍሪካ ሻምፒዮንስ ሊግ የቅድመ ማጣሪያ የመጀመሪያ ጨዋታውን ከደቡብ ሱዳኑ አል ሰላም ዋሁ ክለብ ጋር እንዲያደርግ የጨዋታ መርኃ ግብር ወጥቶለት የነበረው ቅዱስ ጊዮርጊስ ተጋጣሚው የደቡብ ሱዳኑ አል ሰላም ዋኡ በጨዋታው ላይ መገኘት ባለመቻሉ ጨዋታውን ማድረግ ሳይችል ቀርቷል። ይህ የደቡብ ሱዳን ቡድን እስከ የጨዋታው ዕለት ጠዋት 3:00 ድረስ አ/አ እንደሚገባ አሳውቆ የነበረ ቢሆንም ባልታወቀ ምክንያት ለጨዋታው ሳይመጣ ቀርቷል። ቢሆንም ግን የካፍ ህግ በሚያዘው መሰረት ተጨዋቾቹ እና የዕለቱ ዳኞች ሜዳ በመገኘት ከክብር እንግዶች ጋር ትውውቅ አድርገው ህጉ እስከ ሚፈቅደው ደቂቃ ድረስ ሜዳ ውስጥ ቆይተው ወደ መልበሻ ቤት አምርተዋል። ይህንንም ተከትሎ ቅ/ጊዮርጊስ በቀጥታ ወደ አንደኛው ዙር እንዲያልፍ አስችሎታል። በአንደኛው ዙርም ከዩጋንዳው ኬሲሲኤ እና ከማዳጋስካሩ ስናፕስ ስፖርት አሸናፊ ጋር የሚጫወት ይሆናል። ሁለቱ ቡድኖች ማዳጋስካር ላይ ተጫውተው ባለሜዳው ስናፕስ ስፖርት 2-1 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል።
የፎቶ ምንጭ: ኑራ ኢማም

አስተያየት ይስጡ